የሠላምና የሀገረ-መንግስት ግንባታ ስራዎች በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥሉ ተጠየቀ
ሀገራችን ኢትዮጵያ የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ ለማፋጠን የተዘረጉ የሠላም እና የሀገረ-መንግስት ግንባታ ስራዎች በተጠናከረ እና በተቀናጀ መልኩ ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተገለፀ። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት “የሀገረ-መንግስት ግንባታ መሰረታዊያን፤ ሀገራዊ ማንነት፣ ሀገራዊ ጥቅሞች እና እሴቶች ለዘላቂ ሠላም” በሚል መሪ ቃል ለባለድርሻ አካላት በቦንጋ ከተማ ስልጠና እየሰጠ ነው። ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባኤ…
