ምክር ቤቱ የአስፈጻሚ ተቋማት የተግባር አፈጻጸም በመገምገም፣ ክፍተቶች በመለየት የህዝብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ እያስቻለ ነዉ:-የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ በታርጫ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በጉባኤው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የምክር ቤቱ ዋና አፌጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ÷ ምክር ቤቱ ባለፊት የበጀት ዓመት ስድስት ወራት የአስፈጻሚ ተቋማት የተግባር አፈጻጸም በመገምገምና ክፍተቶችን በመለየት የህዝብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የበኩሉን ሚና መወጣቱን ገልጸዋል። የታችኛው…
