የክልሉ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት 47ኛ መደበኛ ስብሰባዉን በሃለላ ኬላ እያካሄደ ይገኛል ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት መስተዳድ ምክር ቤት ዛሬ በሃላላ ኬላ 47ኛዉ መደበኛ ስብሰባ እያካሄደ ነዉ። መስተዳድር ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባዉ የክልሉን መንግስት አስፈጻሚ ተቋማት የመጀመሪያ ስድስት ወራት አፈጻጸም የሚገመገም ሲሆን ሌሎች አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ዉሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።

Read More

“የውኒ ወንዝ ሰው ከመብላት፣ ሰው ወደ ማብላት ተሸጋግሯል” – የገንዶ ነዋሪዎች

በኢትዮጵያ የስንዴ ልማትን “በመስኖ ላይ የተመሰረተ የስንዴ ምርት ከውጭ ከመቀበል ወደ ውጭ ለመላክ የሚደረግ ሽግግር” በሚል መሪ ቃል የተጀመረው የመስኖ ስንዴ ልማት ሥራ ውጤታማ እየኾነ እንደሚገኝ ከግብርና ሚኒስትር የተገኘው መረጃ ያመለክታል። በክልላችን ተጨባጭ፣ በክልሉ ምሥረታ ወቅት የመስኖ አውታር ከነበረበት አነስተኛ ሽፋን አሁን ላይ የክልሉ መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት ትርጉም ባለው መልኩ መሻሻል አሳይቷል። ምንም…

Read More

የማጃንግ ብሔረሰብ የባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየምለማካሄድ ዝግጅቱ ተጠናቋል። ኮሚቴዉ

የማጃንግ ብሔረሰብን የቀደሙ የባህል እሴቶችና ቋንቋ ለማነቃቃት እና ለልማት ለማዋል ያለመ ታላቅ የባህልና የቋንቋ ሲምፖዚየም የካቲት 4 እና 5 በቴፒ ከተማ እንደሚካሄድ የዝግጅቱ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዮሐንስ በንዲ ገለጹ። አቶ ዮሐንስ እንደገለጹት፣ ለሲምፖዚየሙ የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በሙሉ ተጠናቀዋል። የሲምፖዚየሙ ዋና ዓላማ ለረዥም ጊዜ ተዘንግተው የነበሩ የማጃንግ ብሔረሰብ ባህላዊ እሴቶችንና የአኗኗር ዘይቤዎችን እንደገና ማንቃት…

Read More

ከ11ሺህ በላይ ማኅበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርግ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት ተመረቀ።

በዳውሮ ዞን ከጪ ወረዳ፣ የከጪ ከተማ የንጹሕ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በገተገኙበት ተመርቋል። በክልሉ መንግሥት የበጀት ድጋፍ የተገነባው የከጪ ከተማ ንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በተገኙበት ተመርቀው ለአግልግሎት ክፍት ሆኗል። ፕሮጀክቱ በከጪ ከተማ ለረጅም ጊዜ ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግርና የህዝብ ጥያቄ ሆኖ የቆየውን…

Read More

ባለፉት 6 ወራት ከ2 ነጥብ 5 ቢልዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ ገለጸ።

የመምሪያው የ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻፀም ግምገማ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው። በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ መንፈቅ 2 ቢሊዮን 572 ሚልዮን 546 ሺህ ብር በላይ ለመሰብሰብ መታቀዱ ይታወሳል። በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ደመላሽ ንጉሴ ፥ ባለፉት 6 ወራት ከመደበኛና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ከ2 ቢሊዮን 578 ሚልዮን 4…

Read More

በክልሉ አዲስ የገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነዉ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት፣ የክልሉ የገቢዎች ቢሮ ባዘጋጀው የገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ በታርጫ ከተማ እያካሄደ ይገኛል። የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ መድረኩን ሲያስጀምሩ እንደገለጹት፤ መንግሥት የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን በማዘመንና ለኢኮኖሚ ዕድገት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል። በመሆኑም…

Read More

የአፍሪካ መሪዎች በአዲስ አበባ – ከውኃ ዋስትና እስከ አዲሱ ትውልድ የፖለቲካ ተሳትፎ

መዲናዋ አዲስ አበባ የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም የ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤን ታስተናግዳለች። ይህ ጉባኤ በአህጉሪቱ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ “አጀንዳ 2063” መሠረት አስተማማኝ የውኃ እና የንፅህና አቅርቦትን በማረጋገጥ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆን፣ ከፍተኛ የአህጉሪቱ መሪዎችም በጉዳዩ ላይ ይመክራሉ። የቅድመ-ጉባኤ መድረኮች እና የውኃ ዋስትና ከዋናው ጉባኤ ቀደም ብሎ ከየካቲት 3 እስከ 6 ቀን 2018…

Read More

በክልሉ የመሠረተ ልማት ተደራሽነት ማሳደግ ተችሏል፦ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

በዳውሮ ዞን ማረቃ ወረዳ አርሶ አደሩን ከዝናብ ጥገኝነት በማላቀቅ በዓመት እስከ ሦስት ጊዜ እንዲያመርት የሚያስችለው የውኒ አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ባገኙበት ተመርቋል። በምረቃው መርሐ-ግብር መልዕክት ያስተላለፉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)÷ ባለፋት የክልሉ ምሥረታ ወቅት በክልሉ የሚስተዋሉ የልማት ክፍተቶችን በመለየትና ትኩረት በማድረግ…

Read More

ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥ ከ280 በላይ አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ አነስተኛ መስኖ መርቀው ከፍቱ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)÷ በዳውሮ ዞን፣ ማረቃ ወረዳ በክልሉ የመስኖ ኤጄንሲ የተሰራውን የውኒ አነስተኛ መስኖ መርቀው ከፍተዋል። ከ144 ሄክታር የማልማት አቅም ያለው የመስኖ ፕሮጀክት የተገነባው ከ75 ሚሊዮን በሚጠጋ የክልል መንግሥት የበጀት ድጋፍ ነው። ፕሮጀክቱ የ5.7 ኪሎሜትር ዋና የውሃ ካናል የመስመር ዝርጋታ እና ሌሎች የስትራክቸርና መካኒካል ሥራዎች ያካተተ ሲሆን…

Read More

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን የካቲት 5 እና 6 እንደሚያካሄድ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ገልፀዋል።

የ2018 ዓ.ም ግማሽ ዓመት የአስፈፃሚ አካላት ስራ ሪፖርትን ጨምሮ ሌሎች አጀንዳዎች በጉባኤው እንደሚቀርቡም አመላክተዋል። ከጉባኤው አስቀድሞ ምክር ቤቱ በቋሚ ኮሚቴና በጽ/ቤት አማካኝነት በግማሽ ዓመት ለማከናወን ካቀዳቸው ተግባራት መካከል በተለይም የድጋፍና ክትትል እንዲሁም የቁጥጥር ስራዎችን በ5ቱም ዘርፍ ሰርቶ ማጠናቀቁን የተከበሩ አፈ-ጉባኤ አሳውቀዋል። በተጨማሪ የቋሚ ኮሚቴ ስራ ሪፖርት ተገምግሞ ግብረ መልስ ተሰጥቷል ብለዋል። ከግምገማው በኋላ እንደ ክልል…

Read More