“ዛሬ በቄለም ወለጋ ዞን ሃዋ ገላን ወረዳ በሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር የለማ የሙዝ እርሻ ከባቢን ጎብኝቻለሁ።
አርሶአደሮች በፍጹም ጽናት፣ ቅንጅት እና ትብብር አካባቢያቸውን በቀየረ ስራ በመመልከቴ ደስ ብሎኛል። የተመለከትነው የእርሻ ስራ፤ የአካባቢ መሬትን እና የውኃ ኃብትን በአግባቡ መጠቀም ከተቻለ ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ማሳያ ነው። ባህላዊ የመስኖ ዘዴዎችን በመጠቀም እና በቅርብ ያለ ኃብትን በሚገባ ጥቅም ላይ በማዋል ማኅበረሰቡ ውጤታማ እና ተስፋ ሰጪ የግብርና ማዕከል መፍጠር ችሏል። በተለይም የመንገድ መሠረተ ልማት…
