የሸበሌ ሪዞርት ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ተጠናቀቀ
የፌዴራል መስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር እና የፕሮጀክቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፣ ከሶማሊ ክልል የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ ሹክሪና ከሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን የተጠናቀቁ የፕሮጀክት ሥራዎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። ኃላፊዎቹ በጉብኝታቸው ወቅት የሸበሌ ሪዞርት ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ መጠናቀቁን ያረጋገጡ ሲሆን፣ ለምረቃ ሥነ ሥርዓት እየተደረገ ያለውን ዝግጅትም ተመልክተዋል። በተጨማሪም፣ በፕሮጀክቱ ግንባታ…
