Trendings

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የቬይትናም ይፋዊ ጉብኝት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሀኖይ ቬይትናም ይፋዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ2025 የፒ4ጂ ቬይትናም ጉባኤ ላይም ይሳተፋሉ። በቆይታቸው ከቬይትናም የፀሃይ ኃይል ማመንጫዎች በማምረት ወደ ውጭ የሚልከውን ቶዮ ሶላር የተባለውን ፋብሪካ ጎብኝተዋል። ድርጅቱ በቅርቡ በሀዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ በመግባት በኢትዮጵያ ሥራ ጀምሯል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርጅቱ ከፀሃይ ኃይል…

Read More

ዓለም አቀፍ የህፃናት ቀን “ህፃናት የሚሉት አላቸው እናዳምጣቸው! ” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ተገለጸ

የዘንድሮ ዓለም አቀፍ የህፃናት ቀን ለማክበር ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገልጿል ፡፡ የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ እንደገለጹት ዓለም አቀፍ የህፃናት ቀን የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ አካል የሆነው የአለም ህጻናት መብቶች ኮንቬንሽን እ.ኤ.አ ኑቬምበር 20/1989 ዓ.ም በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባዔ ፀድቆ በስራ ላይ እንዲውል…

Read More

ሠልጣኝ አመራሮች በጊምቦ ወረዳ በውሽውሽ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ይገኛሉ

‘በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እምርታ” በሚል ሃሳብ ላለፉት ተከታታይ ቀናት ስልጠና ላይ የነበሩት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል 2ኛዉ ዙር ሀገር ዓቀፍ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በጊምቦ ወረዳ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኘ ነው። በጉብኝቱ በግል አልሚ ባለሀብ አቶ ድንቃለም አደመ እየለማ ያለ የወተት ላሞችን፣ የማታፓ ምቺት የቡና ኢንዱስትሪ እና በአርሶ አደሮች እየለማ ያለውን…

Read More

በኮንታ ዞን አመያ ከተማ መጋቢት 24 ለውጥ ያመጣቸውን ውጤቶችን የሚደግፍ የድጋፍ ሰልፍ በደማቅ ሁኔታ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ሰልፈኞቹ ‘መጋቢት 24 የኢትዮጵያ የብልፅግና ጉዞ የታወጀበት ታሪካዊ ቀን ነው’፤ ‘የመጋቢት 24 ለውጥ በአዲሱ ትውልድ አዲስ ተስፋ፣ አዲስ ምዕራፍ የተሰነቀበት ነው’ እና የመሳሰሉ መፈክሮችን አስተጋብተዋል። በሰልፉ የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች በፈረስና በተሽከርካሪዎች እንዲሁም በባህላዊ ጭፈራና ፖሊሳዊ ትርዒት ታጅበው ተሳትፈዋል።

Read More

የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ለውጥ በማረጋገጥ የአድዋ ድልን ማጽናት እንደሚገባ ተገለጸ

129ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል!” በሚል መርህ ቃል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቦንጋ ከተማ በድምቀት ተከብሯል። በዓሉን በሚመለከት በቀረበው ፓናል ውይይት ሀሳብ የሰጡት የክብረ በዓሉ ተሳታፊዎች የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ለውጥ በማረጋገጥ የአድዋ ድልን በትውልድ ውስጥ ማጽናት እንደሚገባ ተናግረዋል። አድዋ የመደማመጥና የመከባበር እንዲሁም በአንድነት የመቆም ውጤት መሆኑን የጠቆሙት የመድረኩ ተሳታፊዎች የአሁኑ ትውልድ፥…

Read More

ኢትዮጵያ በተመድ የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ለ3ኛ ጊዜ አባል ሆና ተመረጠች

ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ ከ2025-2027 በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለሦስተኛ ጊዜ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባል ሆና ተመረጠች፡፡ ኢትዮጵያ ለሦስተኛ ዙር የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባል በመሆን የተመረጠቸው በ79ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ነው፡፡ ቀደም ሲል በፈረንጆቹ ከ2013 እስከ 2015 እና ከ2016 እስከ 2018 ባለው ጊዜ ኢትዮጵያ የምክር ቤቱ አባል በመሆን ማገልገሏ ይታወሳል፡፡ አሁን ደግሞ ለሦስትኛ…

Read More

ሪፖርታዥ

በክልሉ የህዝብ ቁጥር ከኢኮኖሚ ዕድገት ጋር የተጣጣመ እንዲሆን መጠነ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ ነው፦ የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ በሀገራችን በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣው የህዝብ ቁጥር ከኢኮኖሚ ዕድገት ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ለማስቻል መንግስት በሥነ-ሕዝብ ጉዳዮች ላይ የመስራትን አስፈላጊነት በመረዳት በ1985 ዓ.ም ብሔራዊ የሥነ-ሕዝብ ፖሊሲ እንዲቀረፅ በማድረግ ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል፡፡ ፖሊሲው ተግባራዊ በተደረገባቸው ባለፉት 32 ዓመታት ከሁለንተናዊ ዕድገት…

Read More

የክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የፎቶግራፍ አውደርእይ አካሄደ ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ በ2016 በክልሉ በመንግሥትና አጋር አካላት የተሰሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን የሚያስቃኝ የፎቶግራፍ ኢግዚቢሽን በታርጫ ከተማ አካሂዷል። የፎቶግራፍ ኢግዚቢሽኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢንጂነር)፣ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ፣የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና…

Read More

ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ውጤታማ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ተቋም መገንባት ሚናው የጎላ መሆኑ ተገለፀ

“የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ሚና ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል በሸካ ዞን የሚገኙ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን አመራሮችና ሠራተኞች ጋር ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ የውይይት መድረክ በማሻ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የዕለቱ የክብር እንግዳ የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ በመክፈቻ ንግግራቸው ሚዲያ በፖለቲካው፣ ኢኮኖሚዊና በማህበራዊ ዘርፎች ውጤታማ ለውጥ እንዲመዘገብ እንዲሁም አካባቢን በማስተዋወቅና መላው ህዝብ የልማት…

Read More