ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በጫካ ፕሮጀክት ችግኝ ተከሉ
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በዛሬው ዕለት በጫካ ፕሮጀክት በመገኘት የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አከናውነዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ታዬ በዛሬው ዕለት ያከናወኑት የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ከፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ሠራተኞች እና አመራሮች ጋር በመሆን ነው፡፡ በመትከል ማንሰራራት በሚል መሪ ሀሳብ የዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እየተካሄደ ሲሆን፤ በመላ ኢትዮጵያ ችግኝ እየተተከለ ይገኛል። #FM
