ከመጋቢት አጋማሽ ጀምሮ እስከ ግንቦት መጨረሻ ድረስ ከባድ የበልግ ዝናብ ልኖር ስለሚችል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ::
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደጋማ አከባቢዎች ከመጋቢት አጋማሽ ጀምሮ እስከ ግንቦት መጨረሻ ድረስ ከባድ የበልግ ዝናብ ልኖር ስለሚችል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ለማ መሠለ አሳስበዋል። የብሔራዊ ሜትሮዎሎጂ መረጃን ዋብ ያደረጉ ዶ/ር ለማ በክልሉ በተለይ በደጋማ አከባቢዎች በሚኖረው ከባድ የበልግ ዝናብ ጎርፍና ናዳ ልኖር እንደሚችልም አስረድተዋል። በተለይ…
