Trendings

BLOGS

“‎ዛሬ በቄለም ወለጋ ዞን ሃዋ ገላን ወረዳ በሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር የለማ የሙዝ እርሻ ከባቢን ጎብኝቻለሁ።‎

አርሶአደሮች በፍጹም ጽናት፣ ቅንጅት እና ትብብር አካባቢያቸውን በቀየረ ስራ በመመልከቴ ደስ ብሎኛል። የተመለከትነው የእርሻ ስራ፤ የአካባቢ መሬትን እና የውኃ ኃብትን በአግባቡ መጠቀም ከተቻለ ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ማሳያ ነው። ባህላዊ የመስኖ ዘዴዎችን በመጠቀም እና በቅርብ ያለ ኃብትን በሚገባ ጥቅም ላይ በማዋል ማኅበረሰቡ ውጤታማ እና ተስፋ ሰጪ የግብርና ማዕከል መፍጠር ችሏል። በተለይም የመንገድ መሠረተ ልማት…

Read More

ምርጫ ለእርስዎ ምን ፋይዳ አለው?

ምርጫ እና የምርጫ ዴሞክራሲ እንደ ሀገርም እንደ ማኅበረሰብም በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ እያንዳንዱ ዜጋ በምርጫ በመሳተፉ በሚከተሉት ወሳኝ ጉዳዮች ራሱንም ሀገሩንም ይጠቅማል፡- የሥልጣን ባለቤትነትን ማረጋገጥ፦ ምርጫ ዜጎች የሀገሪቱ የሥልጣን ምንጭ መሆናቸውን በተግባር የሚያሳዩበት መንገድ ነው። አንድ ዜጋ በሰጠው ድምፅ የሀገሪቱን ዕጣ ፈንታ የመወሰን አቅም ይኖረዋል። የመወሰን ነፃነትና ክብር፦ በነፃነት የመምረጥ መብት የግለሰብን ሰብዓዊ ክብርና ነፃነት ያረጋግጣል።…

Read More

የብልጽግና ጉዞውን ዕውን ለማድረግ የሲቭል ሰርቪስ ሪፎርም በተቀመጠው አሠራር ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የፋይናንስና ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲ ላይ ለአመራርና ባለሙያዎች ስልጠና በቦንጋ እየሰጠ ይገኛል። በስልጠናው መድረክ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ምክትል ኃላፊና ፊዝካል ፖሊሲና መንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ዘርፍ ሀላፊ አቶ መለሠ ኡሮ የብልጽግና ጉዞውን ዕውን ለማድረግ በሀገር ደረጃ ብዙ የሪፎርም ስራዎች ሲከናወኑ መቆየቱን ገልጸዋል። ለዚህም ስኬታማነት…

Read More

በኢንዱስትሪዉም ሆነ በቴክኖሎጂዉ ዘርፍ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፊት እንዲወጣ ሁሉም በቁርጠኝነት መሥራት እንዳለበት ተጠቆመ።

‎የክልሉ ኢንዱስትሪ እና ኢኖቬሽን ቢሮ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በቴፒ ከተማ የ2018 በጀት ዓመት 6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ገምግሟል። ‎የገጠር ኢንዱስትራላዜሽን ሥራ ማጠናከር ፣ የዘርፉ ክፍተቶችን በማረም ለኢንዱስትሪ ሽግግር ፣ አዲስ በማቋቋም ረገድ፣ ነባሩን ኢንዱስትሪ ለማጠናከር በትኩረት ልሰራ አንደሚገባ የቢሮ ምክትል ሀላፊና የኢንዱስትሪ ዘርፍ ሀላፊ ወይዘሮ ብርቅነሽ ሻንቆ ተናግረዋል። ‎በአካባቢ ምርቶች ላይ እሴቶችን ጨምሮ ከመስራት አንጻር…

Read More

የቤንች ሸኮ ዞን ምክር ቤት 12ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ።

የቤንች ሸኮ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል። ​የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ጌድዮን ኮስታብ ጉባኤውን ሲከፍቱ ባስተላለፉት መልዕክት ምክር ቤቱ በሕገ-መንግሥቱ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የሕግ ማውጣት፣ የክትትልና ቁጥጥር ሥራዎችን በማከናወን የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት ሲሠራ መቆየቱን ገልጸዋል። ​የሕግ አውጪው፣ የአስፈጻሚውና የሕግ ተርጓሚው አካላት የ2018…

Read More

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሐዊ እና ገለልተኛ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ዳኞች ሚናቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል – የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሐዊ እና ገለልተኛ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ዳኞች ሚናቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ አሳስበዋል። የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር ከምርጫ ጉዳዮች ጋር በተያያዙ በሚመጡ ቅሬታዎች የአፈታት ዘዴ ላይ ለፌደራል እና ለክልል ዳኞች ስልጠና እየሰጠ ነው። ምርጫው ነፃ እና ገለልተኛ እንዲሆን ተቋማዊ…

Read More

ኢትዮጵያ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፉን የምትገነባ እና የምትመራ እንድትሆን ለማድረግ እየተሰራ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

ኢትዮጵያ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘመን ተመልካች ብቻ ሳትሆን ዘርፉን የምትገነባ እና የምትመራ እንድትሆን ለማድረግ እየተሰራ ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ ፖድ (Al UniPod) የፈጠራ ማዕከልን ስራ አስጀምረዋል። ኢትዮጵያ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘመን ተመልካች ብቻ ሳትሆን ዘርፉን የምትገነባ፣ አስተዋጽኦ የምታበረክትና የምትመራ እንዲሁም ወደፊት ለመራመድ አዲስ ምዕራፍ የምትከፍትበት መሆኑን…

Read More

#ሪፖርታዥ

በክልሉ የሰንበት ገበያዎችን በማቋቋም የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው መንግስት የኑሮ ዉድነትን ለማረጋጋት አዳዲስ መመሪያ በማዘጋጀትና የተለያዩ ፖሊሲዎችን በመቅረጽ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል። በዚህም የኑሮ ውድነትን በማረጋጋት የማሕበረሰቡን ኑሮ ጫና ማቃለል እንዲያስችል የሰንበት ገበያዎች ተቋቁመው ማሕበረሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን እየተሰራ ነው። ሰንበት ገበያው የተለያዩ መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶችን ከአምራቾች ወደ ሸማቹ ቀጥታ በማድረስ የዋጋ ጭማሪን ለመቆጣጠር…

Read More

የክልሉ ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ምክር ቤት በታርጫ ከተማ እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን አጽድቋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ያቀረባቸው የተለያዩ የሥራ ክፍሎች ላይ ሹመት ምክር ቤቱ ተቀብሎ በሙሉ ድምፅ አአድቋል። በዚህም መሠረት 1-አቶ ንጉሴ ወ/ጊዮርጊስ:-የክልሉ ሰው ሀብት ልማትና ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ 2ኛ -ረዳት…

Read More

የክልሉ ምክርቤት እያካሄደ ባለው ጉባኤ የቀረበዉን ሞሽን መርምሮ አጸደቀ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ በታርጫ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። ሁለተኛ ቀኑን በያዘው የክልሉ ምክር ቤት ወደ ከተማ የተካለሉ ቀበሌዎች ሞሽን መርምሮ ያጸደቀ ሲሆን ቀበሌዎቹ በክልሉ ስር ባሉት ቤንች ሸኮ እና ሸካ ዞኖች ወደ ከተማ ቀበሌ መዋቅሮች የተካለሉት ናቸው። በሸካ ዞን ወደ ቴፒ ከተማ ወደ…

Read More