ቱሪዝም እንጀራ ነው፤ የሥራ ዕድል ፈጣሪም ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቱሪዝም ከፍተኛ የሥራ ዕድል የሚፈጠርበት ኢንዱስትሪ መሆኑን ስለምናውቅ የመዳረሻ ልማት ሥራዎችን በልዩ ትኩረት እያከናወንን ነው አሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ቱሪዝምን በተመለከተው ማብራሪያቸውም÷ ቱሪዝምን በሚመለከት የመዳረሻ ልማት በልዩ ትኩረት እየተሠራ ነው…
