Trendings

BLOGS

በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ፍላጎትን የማሳኪያ ስልት ልምምድ ሰላምን እየፈተነ ነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ባለፉት 50 እና 60 ዓመታት ሃሳብ ይዞ በሃሳብ አሸንፎ ስልጣን የመያዝ ልምምዱ ያልታየ በመሆኑ እንደባህልም እየተወሰደ ያለው የፖለቲካ ፍላጎትን በጠብመንጃ የማሳካት ፍላጎት አንዱ አደገኛ ስብራት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት የሰላም ችግር መሰረቱ የፖለቲካ ፍላጎት ማሳኪያ መንገድ ላይ ያለው ልምምድ መሆኑን…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ሠላምና ፀጥታን በተመለከተ ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፍላጎት የማሳኪያ ስልት (ልምምድ) ችግር አለበት፤ በዚህም ከውይይት ይልቅ ጠመንጃ ማንሳትን ያስቀደመ መሆኑ ትክክል አለመሆኑን አንስተዋል፡፡ በጦርነት የሚገኝ ጥቅም የለም፤ ጥቅም ያለው ከሠላም ነው፤ ይህን ሁልጊዜም መገንዘብና መኖር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ከሸኔ ጋር የተካሄደው ድርድር ለሕዝብ ይፋ የምናደርገው የተጨበጠ ጉዳይ ስለሌለ ነው ይፋ ያልተደረገው፤ በቀጣይ ተጨባጭ ጉዳይ ሲኖር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይፋ ይደረጋል፡፡ ከሽምቅ ተዋጊ…

Read More

የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እስካሁን ያቀረቧቸው ዋና ዋና ጥያቄዎች

ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ጋር የተደረገው ንግግር ያልተሳካው በምን ምክንያት ነው፤ በአማራ ክልል የተወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል፤ የአማራ ክልል ነባራዊ ሁኔታ ከውጭ ሃይሎች ጣልቃ ገብነት ምን ያህል የጸዳ ነው፤ መንግስት የተዛቡ ችግሮችን ለማረምና አሰባሳቢ ትርክት ለመገንባት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን የተመለከተ ማብራሪያ ቢሰጥ፤ በመንግስትና በፓርቲ ውስጥ ያሉ ዋልታ ረገጥ አስተሳሰቦች ያላቸው ተዋንያንን ለማስተካከል…

Read More

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ መካሄድ ጀመረ!

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ማካሄድ ጀምሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምክር ቤት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ምክር ቤቱ፤ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 55 (17) በተቀመጠውና በምክር ቤቱ የአሠራር እና የአባላት ስነምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 መሠረት፤ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)…

Read More

በጋራ ለሠሩ መሪዎች ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ምሥጋና አቀረቡ::

የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በባሕር ዳር ከተማ ከእርሳቸው ጋር ተገኝተው ሕዝባዊ ውይይቱን ለመሩት የሶማሌ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ እና ለመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትሩ ተሥፋዬ በልጂጌ የክብር ካባ አልብሰዋል። ርእሰ መስተዳድር አረጋ “ወንድሜ ሙስጦፌ በሶማሌ ክልል የሚኖሩ ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች እኩል ተከብረው እና ደኅንነታቸው ተጠብቆ እንዲሠሩ እና እንዲኖሩ ያስቻሉ መሪ ናቸው” ሲሉ ተናግረዋል። አማራ…

Read More

በቦስተን የኒው ባላንስ የቤት ውስጥ ውድድር ጉዳፍ ፀጋይና ለሜቻ ግርማ አሸነፉ::

በቦስተን የኒው ባላንስ የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር ጉዳፍ ፀጋይ እና ለሜቻ ግርማ ውድድሩን በበላይነት አጠናቅቀዋል፡፡ በ1 ሺህ 500 ሜትር የተወዳደረችው ጉዳፍ ፀጋይ ርቀቱን በ3 ደቂቃ 58 ሰከንድ ከ11 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ቀዳሚ ሆናለች፡፡ በዚሁ ርቀት የ18 ዓመቷ አትሌት ብርቄ ሀየሎም 3 ደቂቃ 58 ሰከንድ ከ43 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት 2ኛ ደረጃን ይዛለች፡፡ ወጣቷ…

Read More

የክልሉ ምክር ቤት ጉባዔ ከጥር 30/2016 ጀምሮ ሊካሄድ ነዉ::

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ምክርቤት 6ኛ ዙር 3ኛ የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባዔ ከፊታችን ጥር 30/2016 እስከ የካቲት 1/2016 ዓ/ም በታርጫ ከተማ እንደሚካሄድ አስታወቀ። ጉባኤውን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የክልሉ ምክርቤት ዋና አፈ ጉባዔ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ለጉባኤው አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል ። በዚህም ለጉባኤው ተሳታፊዎች ጥሪ መተላለፉን አፈጉባዔ ወንድሙ ኩርታ…

Read More

ኢትዮጵያን ለዜጎቿ ምቹ ማድረግ የሚያስችሉ አስደናቂ የልማት ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ መሆኑን አይተናል – ሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን::

ኢትዮጵያን ለአሁኑም ይሁን ለቀጣዩ ትውልድ የተመቸች ሀገር ማድረግ የሚያስችሉ የልማትና ግንባታ ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ መሆኑን መመልከታቸውን ወደ ሀገር ቤት የገቡ ሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን ተናገሩ። በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚኖሩ ሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን ከታህሳስ 20 ቀን 2016 እስከ መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም በሶስት ዙር ወደ ሀገር ቤት እንዲመጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል። የመጀመሪያው…

Read More

በክልሉ የተገኘዉን ሠላም ዘላቂነት የማጽናት ትልም!

ሠላም ለሁሉም ነገር መሠረት ነው፡፡ ወጥቶ ለመግባት፣አርሶ ለመብላት፣ወልዶ ለመሳም፣ተምሮ ለመጨረስ፣ተኝቶ ለመታከም በአጠቃላይ ለሰዉ ልጆች ብቻ ሳይሆን ህይወት ላለዉ ነገር ሁሉ ሰላም ወሳኝ መሣሪያ ነዉ።ሠላም በእጃችን ያለ ትልቅ ዉድ ሃብት ነዉ።የቀዬዉ ሰዉ ጧት ማልዶ ለጉዳዩ ሲወጣ“አቤቱ በሠላም አዉለኝ”የሚለዉ የሠላምን ዋጋ ጠንቅቆ ስለሚረዳ ነዉ። በሠላም ወጥቶ መመለስ ምኑን ያህል ጣፋጭ እንደሆነ ስለሚረዳ ነዉ።ሠላም የትም ያለ፣ከሌላ ቦታ የሚገኝ…

Read More

የማህበረሰቡን ጤና ለመጠበቅ የ15 ዓመት የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር ተገብቷል:-አቶ ኢብራሂም ተማም

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የ2016 ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ነዉ። ጊዜውን የዋጀ ፍትሐዊነቱንና ጥራቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ ትኩረት የሚሰጠው ተግባር መሆኑም ተገልጿል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የጤና ተደራሽነትን ፣ጥራትንና ፍትሃዊነትን በሁሉም ደረጃ በማረጋገጥ የእናቶችንና የጨቅላ ህጻናትን ሞት ለመቀነስ ትኩረት በማድረግ ሲሰራ ቆይቷል። የዳውሮ…

Read More