በክልሉ የቪዲዮ ኮንፈረንስ አገልግሎት በቅርቡ እንደሚጀመር የክልሉ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ቢሮ አስታወቀ።
ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከክልሉ መንግስት ጋር በትብብር የተገጠሙ መሆናቸውም ተገልጿል። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የብዝሃ ማዕከላት አደረጃጀት ተዘርግቶ ተግባራዊ መደረግ ከጀመረ ሁለት ዓመታትን አስቆጥሯል ። በክልሉ አራት ብዝሃ ከተሞችና ሁለት ተደራሽ ከተሞች ተቋቁመው የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለማህበረሰቡ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ የክልሉ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ቢሮ አስታውቋል። የቢሮው ኃላፊ አቶ ተስፋዬ…
