የልማት ክፍተቶችን ለመፍታት በተሰሩ ሥራዎች ውጤቶች እየተመዘገቡ ይገኛሉ :- ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በምዕራብ ኦሞ ዞን የባቹማ ኮንስትራክሽን እና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል። በምረቃው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እንደገለጹ፤ በክልሉ በመንግሥትና ፓርቲው መሪነት ባለፉት ዓመታት የልማት ውስንነት ባለባቸው አከባቢዎች የልማት ክፍተቶችን በመፍታት ረገድ ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል። በተለያዩ ምክንያቶች ፍትሃዊ የልማት ሥርጭት ባልተካሄደባቸው…
