ባለፉት 5 ወራት የትራፊክ ደንብ በተላለፉ 17 ሺህ 951 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና የትራፊክ አደጋ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር አስናቀ አፍቴ የትራፊክ አደጋ መከላከልና የታርፍ ቁጥጥር ስርዓቱን ለማሻሻል በርካታ ውጤታማ ተግባራት በማከናወን ላይ እንገኛለን ብለዋል። ከዚህ በፊት የታርፍ ቀጥጥሩም ይሁን የትራፊክ አደጋ መከላከሉና የድጋፍና ክትትል ሂደቱ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ በርካታ ውስንነቶች ያለው መሆኑን ያነሱት ኃላፊው ይህንን ለመቅረፍ ባለፉት ስድስት…
