ከምንም ተነስተው ለከተማ ቤት ባለቤትነት የበቁት የ’አቦ’ ቡና አምራቾች የስኬት ታሪክ
በአንድ ወቅት መሠረታዊ ፍላጎታቸውን ለማሟላት ይቸገሩ የነበሩ የዳውሮ ዞን አርሶ አደሮች፣ ዛሬ በቡና ልማት ተደራጅተው ህይወታቸውን ከመቀየር አልፈው በከተማ ውስጥ ቤት እስከመግዛት የደረሰ የስኬት ጉዞ ላይ መሆናቸውን አስታወቁ። ይህ ታሪክ የመደራጀት ኃይልና የሥራ ትጋት ምን ያህል ለውጥ እንደሚያመጣ በተግባር ያሳየው የ”አቦ ቡና አምራቾች ህብረት ሥራ ማህበር” ነው። የስኬቱ መነሻ ታሪኩ የሚጀምረው 20 አርሶ አደሮች (10ሩ…
