በቡና ምርት ጥራት፣ አቅርቦት እና በግብይት ስርዓቱ ላይ በትኩረት በመስራት ቡናን ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ እየሰራ እንደሚገኝ የክልሉ ቡና ሻይ ቅመማ ቅመም ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
ባለስልጣኑ የታጠበ ቡና ምርት አዘገጃጀት እና ጥራት አጠባበቅ ላይ ከካፋ ዞን ለተውጣጡ የግብርና ባለሙያዎች እና ኢንዱስትሪ ባለቤቶች በቦንጋ ከተማ ስለጠና ሰጥቷል። በስልጠናው በታጠበ ቡና ምርት ዝግጅትና ጥራት አጠባበቅ ፣ በቡና ግብይት አሰራር እንዲሁም የታጠበ ቡና ምርት አዘገጃጀት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቡና ሻይ ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አስራት…
