28ኛው የአድዋ ድል መታሠቢያ በአልን ለማክበር የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ፍፁም ሠላማዊ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል አስታወቀ።
የፀጥታና ደህነት የጋራ ግብረ ሃይሉ የፊታችን የካቲት 23 ቀን 2016 ዓ.ም የሚከበረው 128ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በአል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር ለማስቻል በወጣው የማስፈፀሚያ እቅድ ላይ በአዲስ አበባ ፖሊስ ሰላም አዳራሽ ላይ ውይይት አድርጓል። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻ ሀላፊ ጀነራል ተስፋዬ አያሌው በውይይቱ ወቅት እንደገለፁት የመላው ኢትዮጵያውያን በዓል የሆነው የአድዋ ድል በአል ሲከበር ምንም…
