Trendings

አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ::

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላርስ ራስሙሰን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል። ሚኒስትሮቹ የሁለቱን ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል። በአህጉራዊና ቀጣናዊ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች እንዲሁም በሌሎች ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ በትብብር መስራት በሚያስችላቸው ሁኔታዎች ላይም ውይይት አድርገዋል። ኢትዮጵያና ዴንማርክ በልማት ትብብር፣ የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን፣ የአየር ንብረት…

Read More

ሙሉ በሙሉ በሴቶች ብቻ የሚመራው በረራ ዛሬ ማታ ወደ ለንደን ጋትዊክ ያቀናል::

በኢትዮጵያ አየር መንገድ በየአመቱ ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን አስመልክቶ ሙሉ በሙሉ በሴቶች ብቻ የሚመራው በረራ ዛሬ ማታ ወደ እንግሊዝ ሀገር ለንደን ጋትዊክ ያቀናል:: ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን ማርች 8 አስመልክቶ በአየር መንገዱ በሴቶች ብቻ የሚመራ ጉዞ ወደተለያዩ መዳረሻዎች የሚበር ሲሆን ዘንድሮም ለ9ኛ ጊዜ “ሴቶችን በማብቃት አፍሪካን ማስተሳሰር” በሚል መሪ ቃል ወደ ለንደን ለሚጓዙ የሴት ልዑካን…

Read More

ኢትዮጵያ በዱባይ እየተካሄደ ባለው ዓለም አቀፍ የፖሊስ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው

ኢትዮጵያ “ደህንነቱ ለተጠበቀ ነገ ዓለም አቀፍ የፖሊስ ኃይል ትብብር” በሚል መሪ ሀሳብ በዱባይ እየተካሄደ ባለው ዓለም አቀፍ የፖሊስ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው። በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የተመራው ልዑክ በፈረንጆቹ ከመጋቢት 5 እስከ 7 ቀን 2024 በዱባይ እየተካሄደ ባለው ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያን ወክለው እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ ልዑካን ቡድኑ በቦታው ሲደርስ በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢፌዲሪ…

Read More

የተቋም ግንባታ ውጥናችን ስኬታማነቱ የሚረጋገጠው በጠንካራ ሴቶች ወሳኝ ተሳትፎ ነው ፡- ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ::

የተቋም ግንባታ ውጥናችን ስኬታማነቱ የሚረጋገጠው በጠንካራ ሴት የሰራዊት አባላት ወሳኝ ተሳትፎ ነው ሲሉ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ ገለጹ፡፡ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን “የሴቶች ተጋድሎ ለሰላም እና ለፍትሕ” በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ መርሐ ግብሮች ተከብሯል። ሌ/ጀ ይልማ መርዳሳ በዚህ ወቅት÷ በዓድዋ አርበኛዋ እቴጌ ጣይቱ፣ በሴት አውሮፕላን አብራሪዋ ሙሉ እመቤትና በሌሎች ሴት…

Read More

የኢትዮጵያ አየር መንገድና የቦይንግ ትብብር የኢትዮጵያና የአሜሪካንን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ያጠናክራል – አምባሳደር ኧርቪን ሆሴ ማሲንጋ::

የኢትዮጵያ አየር መንገድና ቦይንግ የደረሱበት የትብብር ደረጃ የኢትዮጵያና የአሜሪካንን ምጣኔ ኃብታዊ ግንኙነት ለማጠናከር ትልት አስተዋጽኦ ያደርጋል ሲሉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ሆሴ ማሲንጋ ገለጹ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአፍሪካ በዓይነታቸው የመጀመሪያ የሆኑ 20 ቦይንግ 777 ኤክስ 9 የተሰኙ ግዙፍ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከቦይንግ ኩባንያ ጋር በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ የመግባቢያ ሥምምነት አድርጓል። በመርኃ-ግብሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ…

Read More

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 በተለያዩ ፕሮግራሞች በቦንጋ ከተማ ተከብሯል::

ማርች 8 ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን በዓለም ለ133ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ48ኛ ጊዜ በክልላችን ደግሞ ለ3ኛ ጊዜ በተለያዩ መርሃግብሮች ተከብሯል። ዕለቱን በማስመልከት ንግግር ያደረጉት በክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሴቶች ሊግ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ውባለም በዛብህ በፈረንጆች አቆጣጠር በ1990ዎቹ ተንሰራፍቶ የነበረው ግፍ፣ጭቆናና በደል በሴቶች ዘንድ በከፍተኛ ሁኔታ ንቅናቄ እንዲያደርጉ መንስኤ መሆኑን ተናግረዋል ። በዚህም ከ15 ሺህ…

Read More

በዋና ዋና ማክሮ ኢኮኖሚ ዘርፎች የተመዘገበው አፈጻጸም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ7 ነጥብ 9 በመቶ እንደሚያድግ አመላካች መሆኑ ተገለፀ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2016 የሁለተኛው ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ማካሄድ ጀምሯል። በመድረኩም ያለፉት ስድስት ወራት የኢኮኖሚ ማህበራዊ እንዲሁም የፍትህና አስተዳደር ዘርፍ አፈጻጸም ሪፖርቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፤ የኢኮኖሚ ዘርፍ አፈጻጸምን ባቀረቡበት ውቅት ኢትዮጵያ በ2015 የ7 ነጥብ 2 በመቶ እድገት ማስመዝገቧን አስታውሰዋል። በተያዘው በጀት…

Read More

በዓለም አቀፉ የወጣቶች ፌስቲቫል ላይ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች እየተሳተፉ ነው::

በሩሲያ ሶቺ ከተማ እየተካሄደ ባለው አለም አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል ላይ ኢትዮጵያውያን እየተሳተፉ ይገኛል። በፌስቲቫሉ ላይ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የተውጣጡ ከ20ሺህ በላይ ወጣቶች እየተሳተፋ ይገኛል። በዚህ ፌስቲቫል ኢትዮጵያውያን ወጣቶችም እየተሳተፋ ሲሆን÷ መድረኩ ወጣቶች ሀገራቸውን እንዲያስተዋውቁ እና እርስ በእርስ ልምድና ተሞክሯቸውን እንዲለዋወጡ የበኩሉን እገዛ እንደሚያደርግ መገለፁን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡ ከፌስቲቫሉ ጎን ለጎን የባህል፣ የስፖርት፣…

Read More

በበርሊን ዓመታዊው ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ኤግዚቢሽን መካሄድ ጀመረ::

በጀርመን በርሊን በየዓመቱ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ኤግዚቢሽን (ITB) ጀምሯል። ይህ ኤግዚቢሽን በመላው ዓለም የሚገኙ ስመጥር የቱሪዝም ካምፓኒዎች እና ሀገራት ያላቸውን መዳረሻ እና የቱሪዝም አገልግሎት የሚያስተዋውቁበት መድረክ ነው። የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በዚህ ኤግዚቢሽን ላይ ተገኝተው፤ ኢትዮጵያ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት እያከናውነቻቸው ያሉ የመዳረሻ ልማቶች እና የቱሪስት መስህቦችን እያስተዋወቁ ይገኛሉ። በተለይም…

Read More

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2016 የሁለተኛው ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም መገምገም ተጀመረ::

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2016 የሁለተኛው ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም መገምገም ጀምሯል። ግምገማው አራቱን የአስተዳደርና ፍትህ፣ የማኅበራዊ፣ የኢኮኖሚያዊ ዘርፎችን በተመለከተ በቀረቡ አፈፃፀሞች ላይ በማተኮር መጀመሩን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መሰል የግምገማ መድረኮች በመንግሥት ተቋማት የመፈፀም ባህልን ለማዳበር የጀመሯቸው መሆናቸው ይታወሳል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Read More