ሁሉም የፋይናንስ ሥርዓቶች ደህንነቸዉ የተጠበቀ በመሆኑ ህብረተሰቡ ያለምንም ስጋት መጠቀም ይችላል-ብሄራዊ ባንክ::
በሁሉም የፋይናንስ ተቋማት የሚገኙ የፋይናንስ ሥርዓቶች ደህንነቸዉ የተጠበቀ በመሆኑ ህብረተሰቡ ያለምንም ስጋት የፋይናንስ አገልግሎቶችን መጠቀም መቀጠል እንደሚችል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አስታወቀ፡፡ ባንኩ አያይዞም አጠቃላይ የፋይናንስ ሥርዓቱ ደህንነት የበለጠ የተጠበቀ፣ አስተማማኝ እና የተረጋጋ ሆኖ እንዲቀጠል አስፈላጊ እርምጃዎችንና የአሠራር ሥርዓት ማሻሻያዎችን መውሰዱን እንደሚቀጥልም አስታውቋል፡፡ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጅታል የባንክ ሥርዓት በጊዜያዊነት መቋረጥን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መግለጫ…
