Trendings

300 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል ያለው የቻይና ኩባንያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች የማምረት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ::

300 ሚሊዮን ዶላር የኢንቨስትመንት ካፒታል ያለው ዌንዡ ኒክሲን ትሬዲንግ ኩባንያ፤ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ወረቀት የማምረት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የኩባንያውን አመራሮች በፅሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። የኩባንያው አመራሮች ስለ ኢንቨስትመንት ዕቅዳቸው ዝርዝር መረጃዎችን ማቅረባቸው ተጠቅሷል። የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ፤ በኮርፖሬሽኑ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ማዕከሎችን፤ማበረታቻዎችን እንዲሁም የመሰረተ ልማትና የአገልግሎት አሰጣጥን…

Read More

ኢትዮጵያ በ13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች ስፖርተኞች ባስመዘገቡት አኩሪ ውጤት ኮርታባቸዋለች::

በ13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች ስፖርተኞች ፈታኙን ሞቃታማ የአየር ንብረት በመቋቋም ባስመዘገቡት አመርቂ ውጤት ኢትዮጵያ ኮርታባቸዋለች ሲሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ ገለጹ። በጋና በተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች ስምንተኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል። ልዑካን ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳን ጨምሮ በሚኒስቴሩ የስፖርት…

Read More

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ያልመለሱ 565 ግለሰቦች የስም ዝርዝር ይፋ አደረገ::

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በባንኩ የሲስተም ማዘመኛ ሥራ ላይ የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. በሂሳብችሁ ከተቀመጠ ገንዘብ ውጭ በሕገወጥ መንገድ ገንዘብ የወሰዳችሁ ግለሰቦች በፈቃደኝነት ሂሳባችሁ በሚገኝበት ቅርንጫፍ በአካል በመቅረብ ወይም ዲጂታል የክፍያ ዘዴን በመጠቀም ገንዘቡን እስከ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ተመላሽ እንዲያደርጉ መጠየቁ ይታወሳል። በዚህ መሰረት 14441 የሚሆኑ ግለሰቦች በተሰጠው ጊዜ…

Read More

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አለልኝ አዘነ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ::

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና የባህርዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች አለልኝ አዘነ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። የባህርዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ እንዳስታወቀው፤ አለልኝ በጉዳት ምክንያት ከቡድኑ ተለይቶ በትውልድ ስፍራው አርባ ምንጭ ለእረፍት የሄደ ሲሆን ትናንት ምሽት በድንገት ህይወቱ አልፏል። አለልኝ የእግርኳስ ህይወቱን በአርባምንጭ ከተማ ክለብ የጀመረ ሲሆን በባህርዳር ከተማ ለሁለት ዓመታት ምርጥ ጊዜ…

Read More

የሴቶችን የአመራርነትና የውሳኔ ሰጪነት አቅም ለማሳደግ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል::

የሴቶችን የአመራርነትና የውሳኔ ሰጪነት አቅም ለማሳደግ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡ በፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት፣ ዩኤን ውሜን እና ቢል ኤንድ ሚሊንዳ ጌትስ ፋውዴሽን አስተባባሪነት ከሁሉም የሀገሪቱ አከባቢዎች ለተወጣጡ ሴቶች በስድስት ዙሮች ሲሰጥ የነበረው “የመካከለኛ አመራር ሴቶች ስልጠና” የማጠቃላይ መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡ በማጠቃላያ መርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፤ በከፍተኛ…

Read More

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አምስት ተጨማሪ የሀገር ውስጥ መዳረሻ ኤርፖርቶችን እየገነባ ነው::

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አምስት ተጨማሪ የሀገር ውስጥ መዳረሻ ኤርፖርቶችን እየገነባ መሆኑን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ገለጹ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ለኢዜአ እንደገለጹት፤ አየር መንገዱ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ መዳረሻዎችን ለማስፋት እየሰራ ነው። የሚያበራቸውን አውሮፕላኖች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ጠቅሰው፤ አሁን ላይ አየር መንገዱ 136 ዓለም አቀፍ እንዲሁም 22…

Read More

የባንኩን ገንዘብ ተመላሽ ያላደረጉ ግለሰቦች መረጃ ላይ ክትትል በማድረግ ተጠያቂነትን ለማስፈን ይሰራል ፦ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት::

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲስተም ብልሽት ባጋጠመው ወቅት ጤናማ ያልሆነ የገንዘብ እንቅስቃሴ ያደረጉ እና በእስካሁኑ ገንዘቡን ተመላሽ ያላደረጉ ግለሰቦች መረጃ ላይ ክትትል በማድረግ ተጠያቂነትን ለማስፈን እንደሚሰራ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ገለፀ፡፡ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጅታል የባንክ ሥርዓት በጊዜያዊነት መቋረጥን አስመልክቶ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ባወጣው መግለጫ፤ በወንጀል ተግባር የተገኘ ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ መጠቀም የህግ ተጠያቂነት እንደሚያስከትል ገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ…

Read More

የኢትዮጵያ የሸማቾች መብት ጥበቃ ማህበራት ጥምረት በይፋ ተመሰረተ

በሸማቾች መብት ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራ የኢትዮጵያ የሸማቾች መብት ጥበቃ ማህበራት ጥምረት በይፋ ተመስርቷል፡፡ ጥምረቱ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴዔታ አቶ እንዳለው መኮንን፣ የንግዱ ዘርፍ ባለድርሻ አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ ተመስርቷል፡፡ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴዔታ አቶ እንዳለው መኮንን በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ ሸማቾች በግብይት ስርዓቱ ላይ ትልቁን ድርሻ ይዘው…

Read More

በባንካችን የደንበኞች የግል አካውንት ላይ የደረሰ ምንም አይነት ጉዳት የለም፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰሞኑን አጋጥሞት የነበረውን የአገልግሎት መቋረጥ ችግር አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ በባንኩ የደንበኞች የግል አካውንት ላይ የደረሰ ምንም አይነት ጉዳት አለመኖሩን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ይፋ አድርገዋል። ባንኩ የውስጥ አሰራሩን ለማዘመን ሲያደርግ በነበረው ሂደት አርብ መጋቢት 6 ሌሊቱን ጤናማ ያልሆነ የገንዘብ እንቅስቃሴ እንደነበረ የጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ የተፈጠረው ክስተት ከሳይበር ጥቃት ጋር የተያያዘ አለመሆኑን አስታውቀዋል፡፡…

Read More

አለመግባባቶች በዘላቂነት እንዲፈቱ ወደ ፈጣሪ መጸለይ ይገባል – የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዚዳንት::

ልዩነቶች እና አለመግባባቶች በዘላቂነት እንዲፈቱ ወደ ፈጣሪ መጸለይ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጣሰው ገብሬ ተናግረዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ የንስሐ፣ የምልጃ እና የምስጋና መርሐ -ግብሩ በኢትዮያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን እና ወደ ኃላ የማይመለስ እርቅ እንዲፈጠር የወንጌል አማኞች የሚጸልዩበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አክለውም መርሐ -ግብሩ ምዕመኑ ለሀገሪቱ ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ “ጌታ እንዲረዳው” የሚማልድበት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡…

Read More