37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጠናቀቀ::
37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎች በማሳለፍ ዛሬ ማለዳ ተጠናቋል። ጉባኤው “ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን አፍሪካዊ ማስተማር፤ የማይበገሩ የትምህርት ስርዓቶች በመገንባት በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ፣ የሕይወት ዘመን፣ ጥራትና አግባብነት ያለው የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋት“ ሕብረቱ ባዘጋጀው የ2024 መሪ ሀሳብ ከቅዳሜ ጀምሮ ሲካሄድ ቆይቷል። በጉባኤው የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ የሕብረቱ ተቋማትና አደረጃጀቶች አመራሮች ተሳትፈዋል።…
