NATIONAL NEWS
በብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ ላይ እየታደሙ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት እህት ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች እንጦጦ ፓርክን ጎበኙ
በብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ እየታደሙ የሚገኙ የጎረቤት ሀገራት እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች እንጦጦ ፓርክን ጎብኝተዋል። ብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን ” ከቃል እስከ ባህል ” በሚል መሪ ሀሳብ ከትላንት ጀምሮ እያካሄደ ይገኛል። በጉባኤ ላይ ለመታደም ከተለያዩ ጎረቤት ሀገራት የመጡ እህት ፓርቲዎች እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች…
የኩባ ኮሚኒስት ፓርቲ ልኡኳን ቡዱን የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት በመገኘት የሁለትዮሽ ውይይት አካሄደ
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ ቡዱኑን ተቀብለው አነጋግረዋል። ልዑክ ቡዱኑ መርተው የመጡት የኩባ ኮሚኒስት ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሜቴ አባል ዩዲ ሜርሴዲስ ኸርናንዴዝ ሲሆኑ የሁለቱን ሀገራት ለዘመናት የዘለቁ ቤተሰባዊነት የተላበሱ ግንኙነቶች የሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርገዋል። የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ…
በተግዳሮቶች ውስጥ እያለፈ ተጨባጭ ለውጥ ያመጣ ፓርቲ ነው ብልፅግና፡- ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)
ብልፅግና ፓርቲ ከበርካታ ተግዳሮቶች ጋር እየታገለ መጠነ ሰፊ ለውጦችን ማምጣቱን የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡ ሚኒስትሩ ሁለተኛውን የብልፅግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ አስመልክቶ ከኢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡ “ብልፅግና የሀሳብ ግልጽነት ያለው ፓርቲ እና ሀሳቡን ተግባራዊ በማድረግ ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ ለውጦችን ማምጣት የቻለ ነው” ብለዋል፡፡ ፓርቲው በአንደኛው መደበኛ ጉባኤው…
ባለፉት ዓመታት የስንዴ ምርታማነት ላይ በትኩረት በመሰራቱ እመርታዊ ለውጥ ማምጣት ተችሏል፡- ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)
ባለፉት ሥድስት ዓመታት የምርምር ተቋማትን በመጠቀም የስንዴ ምርታማነት ላይ በትኩረት በመሰራቱ ተጨባጭ እመርታዊ ለውጥ ማምጣት መቻሉን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገልጸዋል። ባለፉት ሥድስት ዓመታት በግብርናው ዘርፍ የተከናወኑ ስራዎችን አስመልክቶ ሃሳባቸውን ያጋሩት የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)፤ በስንዴ ልማት ከዚህ ቀደም ከነበረው አሰራር በመውጣት የምርምር ተቋማትን በመጠቀም በዕውቀት እና በእቅድ በተሰራው ስራ እመርታዊ ለውጥ መገኘቱን…
የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ በስድስት ወራት ውስጥ ከ46 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘ
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ በግማሽ ዓመቱ ከተለያዩ ምንጮች 46 ነጥብ 7 ቢልዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገለፀ። የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ በሪሶ አመሎ(ዶ/ር) የ2017 የስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ላይ በሰጡት ተቋሙ በስድስት ወራት ውስጥ በሺፒንግ አገልግሎት ከሁለት ሚልዮን ቶን በላይ ጭነት በባህር ማጓጓዙን ገልጸዋል። በዩኒሞዳል የትራንስፖርት ስርዓት ከ654 ሺህ ቶን በላይ የገቢ እና ከ174 ሺህ ቶን…
ብልጽግና ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የተለያዩ አገራት የፓርቲ አመራሮች አዲስ አበባ እየገቡ ነው
በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ የተለያዩ ሀገራት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች አዲስ አበባ መግባታቸውን ቀጥለዋል። በዚህም የብሪክስ አባል ሀገር እህት ፓርቲ የሩሲያው ዩናይትድ ራሺያ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ዲ .ኤ ሜዴቭዴቭ፣ የካዛኪስታኑ አማናት ፓርቲ እና የሀገሪቱ ፓርላማ የታችኛው ምክር ቤት አባል ሳማት ኑር ታተዛ፣ የኩባው ኮሚኒስት ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሜቴ አባል ዩዲ ሜርሴዲስ ኸርናንዴዝ፣ የቱርኬሚስታን ዲሞክራቲክ ፓርቲ…
ብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከዛሬ ጀምሮ ያካሂዳል
ብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ‘ከቃል እስከ ባህል’ በሚል መሪ ሀሳብ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት ያካሂዳል። የፓርቲው ዓለም አቀፍና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት፤ ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በሚካሄደው የፓርቲው 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በርካታ ውሳኔዎች ይወሰናሉ። በተጨማሪም ወሳኝ አቅጣጫዎች የሚተላለፍበት እንደሚሆን አመልክተዋል። በአዲስ አበባ ከዛሬ ጀምሮ እስከ…
በአጭር ጊዜ የተጠናቀቁ የአዲስ አበባ ከተማ ፕሮጀክቶች የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ያስቻሉ ናቸው- ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች
በለውጡ ዓመታት ከቃል ወደ ተግባር መሸጋገር ያስቻሉ እና በአጭር ጊዜ የተጠናቀቁ የአዲስ አበባ ከተማ ፕሮጀክቶች የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ያስቻሉ መሆናቸውን መመልከት እንደቻሉ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ተናገሩ፡፡ የመንግስት የስራ ኃላፊዎቹ ይህንን ያሉት ጉባኤውን በማስመልከት ባለፉት የለውጥ አመታት በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን በጎበኙበት ወቅት ነው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 3 ዓመታት የተከናወኑ ተጨባጭ…
የአዲስ አበባ የለውጥ ጉዞ አስደንቆኛል- ዌላርስ ጋሳማጌራ
አዲስ አበባ በአስደናቂ የለውጥ ጉዞ ላይ እንደምትገኝ መመልከታቸውን የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር ፓርቲ ዋና ጸሃፊ ዌላርስ ጋሳማጌራ ገለጹ። የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር ፓርቲ ዋና ጸሃፊ ዌላርስ ጋሳማጌራ የአንድነት ፓርክን ጎብኝተዋል። ብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ” ከቃል እስከ ባህል ” በሚል መሪ ሃሳብ ከጥር 23 እስከ 25 በአዲስ አበባ ያካሄዳል። በጉባኤ ላይ ለመታደም አዲስ አበባ ከገቡ የውጭ…
