ብልፅግና ፓርቲ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ተጨባጭ ውጤት አስመዝግቧል – ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)
ብልፅግና ፓርቲ በመጀመሪያ ጉባኤው በገባው ቃል መሰረት የሴቶች ህፃናትና ወጣቶችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገቡን የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ሚኒስትሯ ፓርቲው በመጀመሪያው ጉባኤ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች የፈጸማቸውን ተግባራት በተመለከተ ለኢዜአ በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት ራዕያችን በ2022 የዜጎች መብትና ጥቅም የተከበረባት፤ ማህበራዊ ጥበቃ የተስፋፋበት የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ…
