አቶ ጸጋዬ ማሞ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አማካሪ ዴኤታ ሆነው ተሾሙ፡፡
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አማካሪ ዴኤታ ሆነው ለተሾሙት ለአቶ ፀጋዬ ማሞ አቀባበል አድርገዋል፡፡ ክቡር አቶ ፀጋዬ ማሞ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል። የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ስኬታማ የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው በማህበራዊ ትስስር ገጹ ተመኝቷል፡፡
