ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ፦ክፍል አንድ
ሀገራዊ ሪፎርምን በተመለከተበተለያዩ ዘርፎች ሲከናወኑ የነበሩ ሪፎርሞችን አጠናቀን ሀገራዊ ማንሰራራት የምንጀምርበት ዘመን የመጀመሪያ ምእራፍ ላይ ተገኝተናል፡፡ በመሆኑም በ2017 በሁሉም ዘርፎች ተጨባጭ ለውጥ የምናስመዘግብ ይሆናል፡፡ ከዚህ አኳያ ከትናንት እሳቤ ወጥተን በጋራ ወደ ነገ መሻገር አለብን፡፡ ኢኮኖሚያዊ እድገትን በተመለከተበ2016 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ 8 ነጥብ 1 በመቶ እድገት ተመዝግቧል፡፡ ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃም ትልቅ ስኬት ነው፡፡ በዘንድሮው በጀት…
