Trendings

ሀገራዊ የኮሙኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን በብቃት ለመምራት የዘርፉን ባለሙያዎች አቅም የማሳደግ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል – ዶክተር ለገሰ ቱሉ::

ሀገራዊ ተልዕኮን በአግባቡ የተረዳና በእውቀት የሚመራ የኮሙኒኬሽን እና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያን ለመፍጠር የአቅም ግንባታ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ገለጹ፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለፌዴራል እና ለክልል የህዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ሲሰጠው የቆየው ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቋል። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ስልጠናው በአምስት ርእሰ…

Read More

ለ50 ሺህ መምህራንና የትምህርት አመራር የብቃት ስልጠና ሊሰጥ ነው::

በመጪው ክረምት ለ50 ሺህ መምህራንና የትምህርት አመራሮች የብቃት ስልጠና እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል ። ስልጠናው የትምህርት ጥራት ችግርን ለመቅረፍና የመምህራን ብቃትን ለማሳደግ ያለመ ሲሆን÷ በተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ይሰጣል ነው የተባለው። በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራን እና የትምህርት አመራር መሪ ስራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ንጋቱ(ዶ/ር) መምህራኑ የሚሰለጥኑት በሚያስተምሩት ትምህርትና በማስተማሪያ ዘዴዎች መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል ። ለ42 ሺህ…

Read More

የግብርናው ዘርፍ ላይ መዋቅራዊ ሽግግር በማድረግ ድህነትን መቀነስ የመንግስት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ ነው – አቶ ተመስገን ጥሩነህ::

የግብርናው ዘርፍ ላይ መዋቅራዊ ሽግግር በማድረግ ድህነትን መቀነስ የመንግስት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ሀገራዊዉ የሌማት ትሩፋት የአንድ ዓመት ተኩል አፈፃፀም የግምገማ መድረክ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ግብርናውን ከበሬ እርሻ ወደ ተቀናጀ ግብርና ቴክኖሎጂ ለማሻገር ከመንግስት ባለፈ የግሉ ዘርፍ እና ምርምሩ…

Read More

ስታርት አፖችን በፋይናንስ መደገፍ የሚያስችሉ አሠራሮች ተዘርግተው ተግባራዊ እየተደረጉ ነው – የኢትዮጵያ ልማት ባንክ::

በኢትዮጵያ በስፋት የተጀመሩ ስታርት አፖችን በፋይናንስ መደገፍ የሚያስችሉ አሠራሮች ተዘርግተው ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አስታወቀ። በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተውን ስታርት አፕ ኢትዮጵያ አውደ-ርዕይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጨምሮ በርካታ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ምሁራንና ተማሪዎች እንዲሁም የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጎብኝተውታል። ከመጋቢት 30 እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ለሕዝብ ዕይታ ክፍት በተደረገው አውደ-ርዕይ በመጀመሪያ ደረጃ…

Read More

የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ የታክስ አስተዳደርን ለመደገፍ የአምስት ዓመት ፕሮጀክት መቅረፁን ገለፀ::

የገቢዎች ሚኒስቴር እና የዓለም ባንክ በፕሮጀክት አተገባበር ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡ በውይይቱ የገቢዎች ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሤ ÷ ሚኒስቴር መ/ቤቱ በ2022ዓ.ም ዘመናዊ የታክስ አስተዳደር ተገንብቶ ሃገራዊ ወጪ በታክስ ገቢ ተሽፍኖ የማየት ራዕይ ሰንቆ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ ይህንንም ራዕይ ከግብ ለማድረስ እንደ ዓለም ባንክ ካሉ ዓለምዓቀፍ ተቋማት ጋር አብሮ መሥራት ትልቅ አቅም ይፈጥራል ያሉት ወ/ሮ ዓይናለም ሚኒስቴር…

Read More

በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮ-አሜሪካ የቢዝነስ እና የኢንቨስትመንት ፎረም ተካሄደ::

ዋሽንግተን ዲ.ሲ.የሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ኤምባሲ ከዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ-አሜሪካ ቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በዋሽንግተን ዲሲ አካሂዷል። የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ በዚህ ጊዜ እንደገለጹት ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተለያዩ የውጭ እና የውስጥ ፈተናዎች ቢገጥሟትም ኢኮኖሚው እነዚህን ተግዳሮቶች ተቋቁሞ አሁንም ዕድገት እያስመዘገበ ነው። የዚህ ዋነኛ ምክንያት ደግሞ በመንግስት እየተተገበረ ያለው መጠነ ሰፊ የሪፎርም ስራና በመሰረተ ልማቶች ላይ…

Read More

ለኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን የምናደርጋቸው ድጋፎች በሃገር ግንባታ ስራችን ላይ አሻራ የምንጥልበት በመሆኑ አስፈላጊውን የቅንጅት ሰራ በጋራ በመስራት ማገዝ ያለብንን የምናግዝ ይሆናል:-የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ::

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ የኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽንን የአራት ወራት የአፈፃፀም ሪፖርት በዳመጡበት ወቅት ለኮሚሽኑ የምናደርጋቸው ድጋፎች በሃገር ግንባታ ስራችን ላይ አሻራ የምንጥልበት በመሆኑ አስፈላጊውን የቅንጅት ስራ በጋራ በመስራት ማገዝ ያለብንን የምናግዝ ይሆናል ብለዋል። የምክክር ኮሚሽኑ ሃላፊነትን በተላበሰ መልኩ ተልዕኮውን ለማሳካት የሚያገጥሙ ችግሮችን በመቋቋም የህዝባችንን ዘላቂ ሰላም ለማስጠበቅ የስራቸውን…

Read More

ስታርት አፕ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችሉ ናቸው፦የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር::

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድትሆን ስታርትአፖች መበራከት እንደሚገባቸው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ። በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢኖቬሽን ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰላምይሁን አደፍርስ ከኢቢሲ ሳይበር ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ስታርትአፕን ለማበረታታት እየተሞከረ መሆኑ በመጥቀስ ቀጣይነት እንዲኖራቸው እየተሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡ የስታርትአፕ ሀሳብ ያላቸው ሁሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ እና ተዘጋጅተው የሚመጡባቸው ምቹ መድረኮች እንዲኖሩ እየተሰራ ይገኛል የሚሉት ኃላፊው…

Read More

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኤጄንሲ ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው::

14ኛው ዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኤጄንሲ ጉባዔ በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አቡ ዳቢ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡ በጉባዔው የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) እና በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ አምባሳደር ዑመር ሁሴን (ዶ/ር) ኢትዮጵያን በመወከል ተሳትፈዋል፡፡ በጉባኤው ከታዳሽ ኃይል እና የአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ በርካታ ሪፖርቶች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ኤምባሲ…

Read More

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ‘አስተውሎት’ በሚል ርዕስ ያዘጋጀውን ፊልም አስመረቀ::

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ‘አስተውሎት’ በሚል ርዕስ ያዘጋጀውን ፊልም አስመርቋል ፡፡ ፊልሙ ትኩረቱን ኢንስቲትዩቱ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ባከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራት እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ አድርጓል፡፡ ፊልሙን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከሰውኛ ፕሮዳክሽን እና ኢንተርቴይንመንት ጋር በመሆን በጋራ አዘጋጅተውታል። በምርቃት ሥነ-ስርዓቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ…

Read More