በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ከ50 ሺ በላይ ለሚሆኑ መምህራንና የትምህርት አመራሮች ስልጠና ይሰጣል- ትምህርት ሚኒስቴር::
በዘንድሮው ዓመት በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የመምህራን የክረምት ስልጠና ከ50 ሺ በላይ መምህራንና የትምህርት አመራሮች ስልጠና እንደሚሠጣቸው ተገለፀ። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንደገለጹት ስልጠናው አሁን እያስተማሩ ያሉ መምህራን በሚያስተምሩት የትምህርት ይዘትና የማስተማሪያ ስነ ዘዴ ላይ ክህሎት እንዲይዙ ያለመ ነው። መምህራኑ በሚያገኙት ስልጠና በሚያስተምሩት ትምህርት ላይ በበቂ ሁኔታ ማስተማር የሚያስችላቸውን ክህሎት እንደሚያገኙ መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።…
