በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የእሳት አደጋ እየተከሰተ በመሆኑ ጥንቃቄ እንዲደረግ የክልሉ ደን፣ አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቁጥጥር ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኢንጂነር አስራት ገብረማርያም አሳሰቡ።
በክልሉ ከሽካ ዞን በስተቀር በአምስት ዞኖች ስፋቱና የጉዳቱ መጠን የተለያየ የደን እሳት ቃጠሎ መከሰቱን አስታውቀዋል። በካፋ ዞን በጠሎ እና በአዲዮ ወረዳዎች አዋሳኝ አካባቢ ደን ላይና በዴቻ ወረዳ ዳኪቲ ቀበሌ እንዲሁም በገዋታ ወረዳ የደን ቃጠሎ ተከስቶ ማህበረሰቡን በማስተባበር ለመቆጣጠር እየተሠራ ነው ብለዋል። በዳውሮ ዞን ማረቃ አደአ፣ ማሪ ወረዳ፣ ታርጫ ዙሪያ ወረዳ እና ሎማ ወረዳ የእሳት ቃጠሎ…
