Trendings

በክልሉ ያለውን ተፈጥሮአዊና ሰብአዊ ሀብቶቻችን ወደ ተጨባጭ ኢኮኖሚ ለመቀየር ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል፡፡ ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የልማት አቅምና ጸጋ መነሻ በማድረግ በተዘጋጀዉ የቀጣይ ሶስት ዓመት ዕቅድ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተጀምሯል። በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) የክልሉ የቀጣይ ሦስት ዓመታት ዕቅዶች ከመደበኛው የአሠራር ስርዓት ለየት ባለ መንገድ ተፈጥሮአዊና ሰብአዊ ሀብቶቻችን ተጠቅመን ወደ ተጨባጭ ኢኮኖሚ ለመቀየር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የክልሉ የቀጣይ…

Read More

129ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ በቦንጋ ከተማ በአካላዊ እንቅስቃሴና ፅዳት ዘመቻ ተካሄደ።

በመርሀ-ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት፥ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር የማታለም ቸኮል በአድዋ አባቶቻችን ያስመዘገቡትን ድል የአሁኑ ትውልድ በልማት መስክ መድገም አለበት ብለዋል። ከተሞች ለኑሮ ምቹ እንዲሆኑ ዘወትር በየሣምንቱ የፅዳት ዘመቻ ማድረግን ህብረተሰቡ ባህል ማድረግ እንደሚገባ ያስገነዘቡት ኢንጅነር የማታለም ንቁ ዜጋ ለልማት ወሳኝ በመሆኑ ስፓርቲዊ እንቅስቃሴ ማዘውተር ይገባል ብሏል። የቦንጋ ከተማ…

Read More

የዘንድሮ የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል የክልሉ ብዝሃ ማዕከል በሆነችው በታርጫ ከተማ ተከብሯል።

129ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ በድምቀት ተከብሯል። የበዓሉ ክብር እንግዳ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም የዓድዋ ድል የመላው የጥቁር ህዝቦች ድል ነው በማለት ይህ ድል ኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሀገር እንድትሆን ያስቻለ ሲሆን በዚህ ድል የተሳተፉ የኢትዮጵያ ጀግኖች መሰዋዕትነት የሚረሳ አይደለም ሲሉ ገልጸዋል። በዓሉ ለኢትዮጵያ ብቻ…

Read More

ዓድዋ የህብረትና የአንድነት ምልክት መሆኑ ተገለፀ

በኮንታ ዞን 129ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል” በሚል መሪ ቃል በፓናል ውይይትና በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል። የዕለቱን መልዕክት ያስተላለፉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አማካሪ አቶ ብርሃኑ ተፈሪ ድሉ ከኢትዮጵያዊያን የወል ታሪኮች መካከል ታላቁ ታሪክና ግዝፈቱም የዓለምን የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ የሰበረ፣ የፀረ-ቅኝ ትግል አቅጣጫን የጠቆመና የታሪክ ቢያኔ የቀየረ ሀቅ ነው ስሉ ተናግረዋል። አቶ ብርሃኑ የአባቶቻችንን…

Read More

የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ለውጥ በማረጋገጥ የአድዋ ድልን ማጽናት እንደሚገባ ተገለጸ

129ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል!” በሚል መርህ ቃል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቦንጋ ከተማ በድምቀት ተከብሯል። በዓሉን በሚመለከት በቀረበው ፓናል ውይይት ሀሳብ የሰጡት የክብረ በዓሉ ተሳታፊዎች የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ለውጥ በማረጋገጥ የአድዋ ድልን በትውልድ ውስጥ ማጽናት እንደሚገባ ተናግረዋል። አድዋ የመደማመጥና የመከባበር እንዲሁም በአንድነት የመቆም ውጤት መሆኑን የጠቆሙት የመድረኩ ተሳታፊዎች የአሁኑ ትውልድ፥…

Read More

አዲሱ ትውልድ የአድዋን ድል በእውነተኛ የሀገር ፍቅር ስሜት ፣ በልማትና ድህነትን ድል በማድረግ ሊደግም ይገባል ፦አቶ ፋጂዮ ሳፒ

129ኛው የአድዋ ድል በዓል መታሰቢያ በፓናል ውይይትና በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዮ ሳፒ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር አድዋ ኢትዮጵያን በአንድነት ፣ በህብረትና በጀግንነት ታሪክ የሰሩበትና መላው አፍሪካን ነጻ ያወጡበት የድል በዓል ነው ብለዋል። አድዋ ለጥቁር የአፍሪካ ህዝቦች የነጻነትና…

Read More

የተነደፉ ኢኒሼቲቮችን ከውጤት ለማድረስ አመራሩና ባለሙያው በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል፦ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ

በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት እና በቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ልማት ዘርፎች ዙሪያ የንቅናቄ መድረክ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል። ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የዛሬውን መድረክ ሲያጠቃልሉ የግብርና ልማት ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ተጠያቂነትን ያሰፈነ አሰራር መከተል ይጠበቅብናል ብለዋል። በዘርፉም ተፈጥሮንና የሰውን አቅም በመጠቀም ይበልጥ ለውጤታማነት መትጋት ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በሌማት ትሩፋት ስራዎች የተሰጠውን ትኩረት ያህል…

Read More

በግንባታ ላይ የሚገኙ የንጹህ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክቶች በፍጥነት ተጠናቀዉ ለአገልግሎት እንዲበቁ እየተሰራ ነው፦ኢንጂነር በየነ በላቸው

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት በ2017 በጀት ዓመት ባለፉት ወራት 61 የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ከ64ሺ በላይ ህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ የክልሉ ውሃ፣ ማዕድና ኢነርጂ ቢሮ ገለጸ። የክልሉ ውሃ፣ ማዕድን እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር በየነ በላቸው የተመራ ልዑክ በቤንች ሸኮ ዞን ሸኮ ወረዳ በግዝመሬት እና ሺሚ ቀበሌዎች በግንባታ ላይ የሚገኘው የንጹህ…

Read More

የሳይበር ደህንነትን የማስጠበቅ ሀገራዊ አቅም እያደገ መጥቷል – የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር

የሳይበር ደህንነትን የማስጠበቅ ሀገራዊ አቅም እያደገ መምጣቱን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ ተናገሩ። ዋና ዳይሬክተሯ በተቋሙ የሪፎርም ስራዎች፣ እየተገኙ ባሉ ውጤቶና ቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በማብራሪያቸውም የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅና የመከላከል አቅምን ማሳደግ የሚያስችሉ በርካታ የለውጥ ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል። ከለውጥ ስራዎቹ መካከል የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ስራ ላይ መዋሉን አስታውሰዋል። ኮምፒውተርን…

Read More

የአንድነታችን አርማ የሆነውን የዓድዋ ድል በኢኮኖሚው መስክ ለመድገም እየሠራን ነው – የታርጫ ከተማ ነዋሪዎች

የኢትዮጵያውያን ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ዓርማ የሆነውን የዓድዋ ድል በኢኮኖሚው መስክ ዳግም ለማስመዝገብ እየሠራን ነው ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው በዳውሮ ዞን የታርጫ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። 129ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል” በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራል። ድሉን በማስመልከት ኢዜአ ያነጋገራቸው በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ነዋሪዎች ዓድዋ የኢትዮጵያውያን ዘመን አይሽሬ ጀግንነት ማሳያ ነው ብለዋል። አቶ በለጠ ባሾ…

Read More