24 ሚሊዮን ብር የፈጀው አዲሱ የጊንቦ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ ግንባታ ተመረቀ
በ2015 ዓመተ-ምህረት በጊንቦ ወረዳ አስተዳደር የበጀት ድጋፍና በማህበረሰቡ ተሳትፎ የተጀመረው ባለ 2 ወለል እና 12 መማሪያ ክፍሎች ያሉት የህንፃ ግንባታ በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡ በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትመህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ፣ የቢሮው ምክትል ኃላፊ ዶክተር ደስታ ገነሜ፣ የካፋ ዞን የመንግስት ዋና…
