የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኮሙኒኬሽን ዘዴ ልምድ በማካፈል ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገለጸ
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኮሙኒኬሽን ዘዴ በልዩ አተያይ ሐሳቦችን፣ የሥራ ተነሳሽነትን የሚፈጥሩ ልምዶችንና ተግባራትን በማካፈል ላይ ያተኮረ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ገለጸ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክልሎች የሚገኙ የሥራ ሪፖርቶችን ለሌሎች የተነሣሽነት ምንጭ እንዲሆኑ ሲያጋሩ መቆየታቸውንና ላለፉት ሰባት ዓመታት ለየት ባለ መንገድ ግልጽነትና ተደራሽነትን በማለም የኮሙኒኬሽን ስራው መከናወኑን ጽ/ቤቱ አስታውቋል፡፡ በዚህ ሂደት የክልሎች የሥራ ለውጦች…
