በአዳማ የተጀመረዉ የስማርት ሲቲ ግንባታ ቀልጣፋ መንግሥታዊ አገልግሎት መስጠት ማስቻሉ ተገለጸ
“ዓላማ ተኮር፣ የተናበበ እና የተቀናጀ የተግባቦት ሥርዓት ለእመርታዊ ዕድገት” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ያለዉ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ የጋራ ጉባኤ ተሳታፊዎች የአዳማ ከተማን “ስማርት አዳማ ፕሮጀክትን” ጎብኝተዋል፡፡ የከተማዋ የዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥ የመንግሥትን አሠራር ሥርዓት ከማዘመኑም በላይ ለማኅበረሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ያስቻለ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር ) ገልጸዋል፡፡ ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተሠሩ ያሉ…
