Trendings

ኢሬቻ:-ፍቅር፣ ሰላምና አንድነት የሚፀናበት ታላቅ እሴት ነው – አቶ ፍቅሬ አማን

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን፣ የኢሬቻ በዓል ፍቅር፣ ሰላም፣ አንድነትና ይቅር ባይነት የሚፀናበት ታላቅ ባህላዊ እሴት መሆኑን ገለጹ። አቶ ፍቅሬ ይህንን የገለጹት ለመላው የኦሮሞ ህዝብና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች የእንኳን ለኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ መልዕክታቸውን ባስተላለፉበት ወቅት ነው። በዓሉ የኦሮሞ ህዝብ የክረምቱን የጨለማ ወቅት አልፎ ወደ ብርሃን ዘመን በሰላም…

Read More

የገቢ አሰባሰብ ስረዓት በማሻሻል የክልሉን ገቢ ማሳደግ ተችሏል፦ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ገቢዎች ቢሮ፣በፍቃደኝነት ግብር የመክፈል ባህል እንዲዳብር ለማስቻል ያለመ የባለድርሻ አካላት ምክክር በሚዛን አማን ከተማ አካሂዷል። የክልሉ ገቢ የመሰብሰብ አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን የጠቆሙት የቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ፥ የገቢ አሰባሰብ ስርዓት በማሻሻል የገቢ አቅምን ትርጉም ባለው መልኩ ማሳደግ መቻሉን ተናግረዋል። በክልሉ የሚገኙ የሚዲያና ኮሚውኒኬሽን ተቋማት፣ የሃይማኖት ተቋማት እንዲሁም…

Read More

የሰቆጣ ቃል ክዳን ማስፋፊያ ፕሮግራም ውጤታማ እንዲሆን ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ከክልሉ የምግብና ስርዓተ ምግብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጋር በመሆን ሲያካሄድ የነበረው የሰቆጣ ቃል ክዳን ፕሮግራም የ2017 ዓ.ም የአፈፃፀም ግምገማና የ2018 የጀት ዓ.ም የዕቅድ ዝግጅት መድረክ ተጠናቋል፡፡ በመድረኩ በፕሮግራሙ የተሰሩ ስራዎች አበረታች መሆኑ ከሪፓርቱ ለመመልከት የተቻለ ሲሆን በስርዓት-ምግብ ችግር የህፃናት መቀንጨርና የመቀጨጭ ለመቀነስ ፕሮግራሙ በታቀፉ ወረዳዎች ትኩረት ተሰጥተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው…

Read More

የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችና የህዝብ ግኑኝነት አመራሮች የገቢ አሰባሰቡ ውጤታማ እንዲኾን የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ገቢዎች ቢሮ፣በፍቃደኝነት ግብር የመክፈል ባህል እንዲዳብር ለማስቻል ያለመ የባለድርሻ አካላት ምክክር በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። የውስጥ ገቢ በአግባቡ በመሰብሰብ የክልሉ ህዝቦች ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ የአስተምህሮ ስራ ወሳኝ መኾኑን ነው የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ በመክፈቻ ንግግራቸው የገለጹት። የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችና የሚዲያ አመራሮች በክልሉ የገቢ አሰባሰብ ሥራው ውጤታማ…

Read More

በክልሉ ለኦዲት ግኝቶች ምላሽ በማይሰጡ ተቋማት ላይ የተጠያቂነትና ህግ የማስከበር ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል፦ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የኦዲት ግኝት አስመላሽ ግብረ-ሀይል በኦዲት ግኝት እርምት አወሳሰድ ላይ የአፈፃፀም ግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ አካሂዷል፡፡ በመድረኩ በክልሉ በቤንች ሸኮና በካፋ ዞን በንግድና ኢንቨስትመንት እና በስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዝ መምሪያ የተደረገውን የክዋኔ እና አካባቢ ኦዲት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡ የክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር አቶ አስራት አበበ ባቀረቡት የሥራ ዕድል…

Read More

የሴቶች፣ ህፃናት፣ አረጋዊያን እና አካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በማስጠበቅ የኢትዮጵያ ልማትን ሀጋረዊ መልክ እንዲኖረው ማስቻል ያስፈልጋል ተባለ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ምክክር ዙሪያ የሴክተር ጉባኤ መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካኸደ ነው። መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ የያዝነው በጀት ዓመት ሀገራችን ለዘመናት ከነበረችበት ታሪካዊና ማህበራዊ ኩስምና ተላቃ የመቻል እና የመወሰን አቅማችንን በብዙ ፕሮጀክቶች ያየንበት በመሆኑ የዝህ…

Read More

ሚዲያው በተደራጀ መንገድ አየር ላይ እንዲወጣ ስራ አመራር ቦርዱ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እያደረገ ይገኛል፦ አቶ ፍቅሬ አማን

‎ ‎የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ስራ አመራር ቦርድ ውይይት በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። ‎በውይይቱ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ፍቅሬ አማን ሚዲያው በተደራጀ መንገድ አየር ላይ እንዲወጣ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ‎አቶ ፍቅሬ አክለውም ክልሉ የሚዲያ ተቋም አስፈላጊነት በመገንዘብ በሰጠው ትኩረት ክልሉ የራሱ ሚዲያ…

Read More

በክልሉ በዘንድሮ ዓመት ከ62 ሺህ በላይ ሄክታር ማሳ በበጋ ስንዴ ልማትና በ1ኛ ዙር መደበኛ መስኖ በተለያዩ ሰብሎች ይለማል፦አቶ ማስረሻ በላቸዉ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ የ2017 ዓ.ም የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትና መደበኛ መስኖ ሥራዎች አፈጻጸም እንዲሁም የ2018 ዕቅድ ዙሪያ የንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በወቅቱ እንደገለጹት፤እንደሀገር በምግብ ራስን መቻል፣ተተኪ ምርት ማምረት እና የምግብ ልዑላዊነት ለማረጋገጥ ሥራዎች በትኩረት እየተከናወነ ይገኛል። በሀገራችን…

Read More

በክልሉ ሠላምን በማጽናት ልማትና እንቨስትመንትን ማስፋፋት እንደሚገባ ተጠቆመ።

“ሠላምን በማጽናት በልማት ማንሰራራት” በሚል መርህ ቃል በኢፌዴሪ የሠላም ሚኒስቴር፤ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሠላምና ፀጥታ መዋቅር የተዘጋጀው ስልጠና በሚዛን አማን ከተማ እየተሰጠ ይገኛል። በስልጠናው መድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ፣ ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ ሀብታሙ አለሙ፥ በክልሉ አለመግባባትና ግጭቶችን ማኅበረሰብን ባሳተፈ ውይይት መፍታት በመቻሉ አወንታዊ ሠላም መስፈኑን ተናግረዋል። የተገኘውን ሠላም ዘላቂነት…

Read More

በክልል ማዕከል አጠቃላይ 59 አመራሮችን ከኃላፊነት የማንሳት፣ የማሸጋሸግ እና በአዲስ መልክ ማደራጀት ሥራ ተሠርቷል፦አቶ ፍቅሬ አማን

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ክልላዊ የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸው በብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት በተቀመጡ አቅጣጫዎች መሠረት ከክልል እስከ ታችኛው መዋቅር ያሉት አመራሮች የግምገማና የምዘና መድረክ በጥብቅ ዲስፕሊን በመምራት አመራሩን በተገቢው መመዘን መቻሉን አስታውሰዋል። ግምገማው የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምን መነሻ በማድረግ የ2018 የፓርቲና…

Read More