‹‹‹‹‹‹ ሪፖርታዥ ››››››
የግብርና ዘርፍ ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት ውስጥ ከሚበረክተው ድርሻ አኳ ከፍተኛውን የሚሸፍንና የኢኮኖሚ መሠረት በመሆን ለማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም ከፍተኛ አስተዋፅዖ የሚያበረክት የኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ ነው። የግብርናው ዘርፍ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በዘላቂነት የማሳደግ እና የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግርን እውን የማድረግ ድርብርብ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል። በመሆኑም በቀጣዮቹ ዓመታት የሚኖረውን ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሀገሪቱን ሕዝብ የመመገብና ሀገራዊ የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ፣ በመካከለኛ…
