ኮሚሽኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አጀንዳዎችን ተረከበ
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በሰባት ክፍሎችና በ64 ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ያዘጋጃቸውን አጀንዳዎች መረከቡን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ አጀንዳዎቹን የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) ከሌሎች ኮሚሽነሮች ጋር በጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ሰለሞን አየለ ከተመራው የምክር ቤቱ የሥራ አስፈፃሚ አባላት ቡድን መረከባቸው ተገልጿል፡፡ መስፍን (ፕ/ር) በዚሁ ወቅት ኮሚሽኑ ከምክር ቤቱ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሞ…
