በክልሉ በበጀት ዓመቱ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን የዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚዎችን እንዲኖሩ ይሰራል
የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም በደቡብ ምዕራብ ክልል በቦንጋ ከተማ ከክልልና ዞን ከፍተኛ አመራሮች ጋር በዲጂታል መታወቂያ የ2018 ዓም የፋይዳ ምዝገባ ዕቅድ እና የክልሉ አሁናዊ የምዝገባ ሂዳት ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሂዷል። የዉይይት መድረኩን የመሩት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን እንዳሉትር፣በ2018 ዓም ለመፈጸም የተያዘዉን የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ዕቅድን ለማሳካት ከመደበኛ ተግባር ባለፈ በንቅናቄ…
“ባለፉት ሶስት ወራት ከ20 የማያንሱ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች በኢትዮጵያ ተካሂደዋል”
ባለፉት ሶስት ወራት ከ20 የማያንሱ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች ተካሂደዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስተርር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ባለፈው ዓመት ዓመቱን ሙሉ 20 ዓለም አቀፍ ኮንፈረሶችን አላካሄድንም፤ ዘንድሮ በሶስት ወር ብቻ 20 የሚደርሱ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶችን አካሂደናል ብለዋል፡፡ በቀጣይም በርካታ ዓለም ዓቀፍ ኮንፈረንሶች በኢትዮጵያ ይካሔዳሉ ሲሉ አመላክተዋል፡፡ የኮሪደር ልማት እና በኢትዮጵያ የተፈጠረው አውድ ዓለም አቀፍ ጎብኚዎችን ኮንፈረንሶችን…
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቦንጋ ከተማ ጥራታቸው የተጠበቁ እና የዘር ምንጫቸው የታወቁ የአትክልት ዘሮች እና ሌሎች ኬሚካሎች ለኤግዚቢሽን ቀረበ
በኤግዚቢሽኑ በርካታ ካምፓኒዎች የተሳተፉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ማርቆስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተለያዩ አትክልት ዘሮች፣ ሚኢረጅ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የጸረ አረምና ጸረ ተባይ ኬሚካል የኬምቴክስ የግብርና ምርቶች፣ ዋይዝ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት የአትክልት ዘር፣ እንዲሁም ሌሎች የተለያዩ ድርጅቶች ምርቶቻቸውን ለእይታ አቅርበዋል። በኤግዚብሽኑ ምርቶቻቸውን ይዘው የቀረቡ የተለያዩ ድርጅቶች ለምርትና ምርታማነት ማደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው ምርቶችን…
የሙስና ትግሉን በዘላቂነት ለማስቀጠል በአሰራር ብቻ የሚመራ ጠንካራ ተቋም መገንባት ይገባል፦ አቶ ንጉሴ ወ/ጊዮርጊስ
”ትውልድን በስነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሰራር” በሚል መሪ ቃል 22ኛ ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ክልላዊ ማጠቃለያ መርሐግብር በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጉሴ ወ/ጊዮርጊስ ሙስና ለሀገር ዕድገት ማነቆ በመሆኑ ሙስናና ብልሹ አሰራርን መታገል እንደሚገባ ተናግረዋል። በክልሉ ህብረተሰቡ ባሳተፈ ትግል ሙስናን የመከላከል አቅም ማሳደግ መቻሉን ጠቁመው በሙስናና ብልሹ…
ከሪበላ ሐይቅ:-ዉብ ተፈጥሮ ማራኪ መዝናኛ
የለውጡ መንግስት ትኩረት ከሰጠባቸው ዘርፎች አንዱ የቱሪዝም ዘርፍ ሲሆን ያንኑ እኒሼቲቭ እያስፋፉ ካሉት አካባቢዎች አንዱ ኮንታ ዞን ነው። በዞኑ ተዝቆ የማያልቁ የቱሪዝም ሀብቶች መካከል አንዱ በኤላ ሃንቻኖ ወረዳ ከሪበላ ባደጉቻ ቀበሌ የሚገኘው ከሪበላ ሐይቅ ነው። ሐይቁ ውብ ቀለም በሚሰጡ ተፈጥሯዊ ጥቅጥቅ ደኖችና ዘንባባ ቀለማት የተሞሸረ በመሆኑ ለአይን ተጨማሪ እፎይታ ይሰጣል። ይህ ውብ ስራ ተፈጥሯዊ ይዞታን…
ለዐይን ሕክምና ተቋማት አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል
መንግስት የዐይን ሕክምና አገልግሎት ለሚሰጡ ተቋማት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ገለጹ። ሚኒስትር ዴኤታው በኪዩር ብላይንድነስ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስፈጻሚ ካትሊን ኦቨርቤይ ከተመራ ልዑካን ቡድን ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል። ዶክተር ደረጀ ኪዩር ብላይንድነስ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ የዐይን ህክምና ላይ ከጤና ሚኒስቴር ጋር ከሚሰሩ ድርጅቶች አንዱ መሆኑን ገልጸው የተቋሙ የሃኪሞች ስልጠና ለዘርፉ ከፍተኛ…
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ55 ሚሊዮን ዶላር ያስገነባውን የኢ-ኮሜርስ ሎጂስቲክስ ማዕከል አስመረቀ::
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ55 ሚሊዮን ዶላር ያስገነባውን ዘመናዊ የኢ-ኮሜርስ ሎጂስቲክስ ማዕከል በዛሬው ዕለት አስመርቋል። አየር መንገዱ በዛሬው ዕለት ያስመረቀው መሠረተ ልማት በአፍሪካ በዓይነቱ የመጀመሪያው ነው ተብሏል። በልዩ ሁኔታ ለኢኮሜርስ ሸቀጦች እንዲሁም ለፖስታ እና ጥቅል መልእክቶች የሎጂስቲክስ አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ ወደ ስራ የሚገባው መሰረተ-ልማት፤ የአፍሪካን የኢኮሜርስ ኢንደስትሪ ዕድገት ከማፋጠኑም ባሻገር፣ አዲስ አበባን በአፍሪካ ብሎም በዓለም…
በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅራቢነት ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም የሚከተሉትን የጦር መኮንኖችን ሹመዋል፦
በጄነራልነት ማዕረግ፦ 1 ሌ/ጄኔራል አለምሸት ደግፌ 2 ሌ/ጄኔራል ደስታ አብቼ 3 ሌ/ጄኔራል ይመር መኮንን 4 ሌ/ጄኔራል ድሪባ መኮንን በሌ/ጄኔራል ማዕረግ፦ 1 ሜ/ጄኔራል ከፍያለዉ አምዴ ተሰማ 2 ሜ/ጄኔራል ክንዱ ገዙ ተገኝ በሜ/ጄኔራል ማዕረግ፦ 1 ብ/ጄኔራል ታደሰ አመሎ ሲኤሳ 2 ብ/ጄኔራል ቡልቲ ታደሰ ክቲላ 3 ብ/ጄኔራል ኃይሉ እንደሻዉ አቶምሳ 4 ብ/ጄኔራል ዋኘዉ አለሜ አያሌዉ 5 ብ/ጄኔራል ነገራ…
አዳዲስ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ወደ ስራ መግባታቸው ለኮንስትራክሽን ዘርፉ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ተባለ
በኢትዮጵያ አዳዲስ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ወደ ስራ መግባታቸው በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለተሰማሩ አልሚዎች ምቹ አጋጣሚ እየፈጠረ መሆኑን ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ። ፕሬዚዳንት ታዬ በድሬዳዋ ከተማ የተገነባውን የፓዮኔር ሲሚንቶ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ማስፋፊያ ፕሮጀክት መርቀዋል። በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ እና በቻይና ባለሃብቶች አጋርነት የተገነባው ፓዮኔር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዕድገት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ አለው።…
