ባለፉት ዓመታት በፍትሕ ዘርፉ መሰረተዊ ለውጦችና ስኬቶች ተመዝግበዋል፡- የፍትሕ ሚኒስትር ሃና አርዓያሥላሴ
ባለፉት 6 ዓመታት የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት በተደረጉ የሕግ እና ተቋማዊ ማሻሻያዎች፣ በፍትሕ ዘርፉ መሰረታዊ ለውጦችና ስኬቶች መመዝገባቸውን የፍትሕ ሚኒስትር ወ/ሮ ሃና አርዓያሥላሴ ገልጸዋል። ሚኒስትሯ በፍትሕ ዘርፉ የተተገበሩ የሪፎርም ስራዎችን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፤ በአጠቃላይ የፍትሕ ሥርዓቱን ለማጠናከር በዘርፉ የነበሩ ክፍተቶችን በመለየት ማሻሻያ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል። ከተሻሻሉ ሕጎች መካከል ለብዙ ቅሬታዎች ምንጭ የነበረውን የሽብር ሕግ በማስተካከልና በማሻሻል…
