የወባ ስርጭትን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ የማህበረሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
በሸካ ዞን የማህበረሰብ አቀፍ የወባ መከላከል ስራዎች እና በወሳኝ የጤና ተግባራት ዙሪያ የባለድርሻ አካላት ንቅናቄ መድረክ በማሻ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። የንቅናቄ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ እንደገለጹት ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ጤናማና አምራች ትውልድ መፍጠር ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው ብለዋል። ወባና ሌሎች በሽታዎችን ከመከላከል ጎን ለጎን ማከምና ማዳን ላይ ትኩረት ሰጥቶ…
