የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት የጅማ ከተማን የተደበቀ ውበት ይበልጥ እንዲፈካ አድርጓል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጅማ የነበራቸውን ቆይታ አስመልከተው በሰጡት ማብራሪ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሃብት የታደለች ሀገር መሆኗን አውስተው÷ ቢሰራባቸው ዓለምን የሚያስደንቁ የተፈጥሮ ጸጋዎች በሁሉም የኢትዮጵያ ጫፍ እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ መደመር የሚለው ሃሳብ ሲጀመር ሶስት ዋና ዋና ምሰሶዎች ላይ የቆመ እንደነበር የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ÷ የመጀመሪያው የኢትዮጵያን ተፈጥሮ፣ ጸጋና ሃብት በውል ማወቅ መቻል ነው ብለዋል፡፡ አሁን ላይ የጅማን…
