በክልሉ ለ3ኛ ጊዜ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረው የብሔረሰቦች ቀን በዓል በድምቀት እንዲከበር ሰፊ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች መከናወናቸው ተገለጸ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ለ3ኛ ጊዜ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረው የብሔረሰቦች ቀን በዓል በድምቀት እንዲከበር ሰፊ ስራዎች መከናወናቸው ተገልጿል። ለበዓሉ ድምቀት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅቶች በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን የገለፁ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ በዓሉ በክልሉ ሁሉም አከባቢዎች ከቀበሌ ጀምሮ በትምህርት ቤቶችና በተለያዩ ቦታዎች በድምቀት እየተከበረ መቆየቱን…
