ሥራ አጥ ወጣቶችን በማህበረሰብ አገልግሎት በማሳተፍ ወደ ሥራ ሽግግር ማስገባት ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ
ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ የኮሙኒኬሽን ፕሮግራም ማዕከል (JHUCCP) በወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራና በማህበራዊ አገልግሎት ወደ ስራ ማሸጋገር ላይ ፕሮጀክቱ በሚዛን አማን ከተማ ስልጠና ሰጥቷል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ እንዳሻው እንደገለፁት በሀገራችን ትኩረት ከተሰጣቸው ዘርፎች የስራ ዕድል ፈጠራ አንዱ መሆኑን ተናግረዋል። የስራ ዕድል በመፍጠር መንግስት ፣የግል ተቋማት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት…
