2016 በጀት ዓመት የኢትዮጵያን ዕድገት ያስቀጠልንበት ዓመት ነው -ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
2016 በጀት ዓመት የኢትዮጵያን ዕድገት ያስቀጠልንበት ዓመት ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ተጠሪነታቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሆኑ አስፈጻሚ ተቋማት የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2017 ዕቅድ የግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የተጠናቀቀው በጀት ዓመት በብዙ መልኩ ስኬት የተመዘገበበት ነበር ብለዋል። በዚህም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ እድገት ማስቀጠል ተችሏል ነው ያሉት። ለሰላም…
