የተራቆቱ አከባቢዎችን ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ባላቸው ችግኞች ለመሸፈን ትኩረት ይደረጋል፦ ዶክተር ኢንጂነር አስራት ገ/ማሪያም
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ደን፣አከባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ አመራሮችና የሬድ ፕላስ ፕሮግራም አስተባባሪዎችና ሠራተኞች ችግኝ ተከሉ። ቤንች ሸኮ ዞን ሰሜን ቤንች ወረዳ ቃሻ ቀበሌ በሬድ ፕላስ ፕሮግራም የተዘጋጁ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን በተዘጋጀው 2 ሺህ ጉድጓድ ላይ ተከለ ተከናውኗል ። በዚሁ ወቅት የክልሉ ደን፣አከባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ኃላፊ…
