በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት የአገልግሎት አቅርቦት ሙሉ በሙሉ ተመልሷል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የተደረሰባቸው ነጥቦች ሙሉ በሙሉ እየተተገበሩ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡ በተለይ የስምምነቱ ዋነኛ ነጥብ የነበረው የመሰረተ ልማት አቅርቦት ጥያቄን መመለስ መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡ በዚህም የመሰረተ ልማት አገልግሎቶች፣ የጊዜያዊ አስተዳደር መንግስት የማቋቋም ጥያቄ እና የተፈናቀሉትን የመመለስ ስራዎች ሙሉ በሙሉ እየተተገበሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በራያ፣ በፀለምት እና ሌሎችም አካባቢዎች ተፈናቃዮችን የመመለስ ስራ…
