የማሻ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታ እስከ ሀምሌ 15/2016 አመተ ምህረት ተጠናቀው ርክክብ እንደሚደረግ የሸካ ዞን አስተዳደር ገለፀ
የዞን አስተዳደር ከክልል ጤና እና ኮንስትራክሽን ቢሮዎች ከተገኙ አካላት እንዲሁም ከሆስፒታሉ ኮንትራክተርና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሆስፒታሉ ያለበትን ደረጃ ገምግሟል። በቦታው ላይ የተገኙት የክልል ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አያለው አደሎ እንደገለፁት የማሻ ሆስፒታል ለብዙ አመታት በተለያዩ ምክንያቶች የዘገየ መሆኑን ጠቁመው በአጭር ግዜ ውስጥ ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት እንዲችል የክልሉ መንግስት በልዩ ትኩረት እየሰራ እንደሚገኝና…
