የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መሰጠት ጀመረ
የ2016 ዓ.ም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መሰጠት ጀምሯል። በዛሬው ዕለት የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች ፈተናቸውን እየወሰዱ መሆኑ ታውቋል፡፡ ፈተናውን በይፋ ያስጀመሩት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)÷ ዛሬ የሚሰጠው ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የበይነ መረብና የወረቀት ፈተና በድብልቅ ነው ብለዋል። በመላ ሀገሪቱ የተጀመረው የበይነ መረብና የወረቀት ፈተና እንደ ሀገር…
