Trendings

Getenesh Gebeyehu

ለአዲዮ ካካ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግምቱ 500 ሺህ ብር የሚጠጋ የደም መመርመሪያ ማሽን ድጋፍ ተደረገ ።

በክልሉ መንግስት የተገዛውን ዘመናዊ የደም መመርመሪያ ማሽን የክልሉ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ አስረክበዋል ። የክልሉ መንግስት የአዲዮ ካካ የመጀመሪያ ሆስፒታል ሲመረቅ ቃል በገባው መሠረት ለሆስፒታሉ መሠረታዊ የህክምና ቁሳቁስ አስፈላጊ መሆኑን በማመን ይኸው ተገዝቶ ማሽን ድጋፍ መደረጉን ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ተናግረዋል ። ሆስፒታሉ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጥ ህብረተሰቡ የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ…

Read More

የበጀት ዓመቱ የግብርና ግብዓት አቅርቦትና የዘር ሽፋን ከፍተኛ ለውጥ የተመዘገበበት ነው – ግርማ አመንቴ(ዶ/ር)

የበጀት ዓመቱ የግብርና ግብዓት አቅርቦትና የዘር ሽፋን ከፍተኛ ለውጥ የተመዘገበበት መሆኑን የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ገለጹ። የበጀት ዓመቱ የመጨረሻ የ100 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል። በመድረኩም የግብርና ስራዎች አፈፃፀም በስፋት ውይይት የተደረገበት መሆኑን የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ገልጸዋል። የ2015/16 የምርት ዘመን ከታቀደው እቅድ ጋር ተቀራራቢ የሆነ ምርት የተሰበሰበበት መሆኑንም አንስተዋል። በተለይም…

Read More

በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች 2 ሺህ የጤና ማዕከላትን መገንባት የሚያስችል ሥምምነት ተፈረመ

በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች 2 ሺህ የጤና ማዕከላትን ለመገንባት የጤና ሚኒስቴርና ሌሎች ሦስት ተቋማት የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራረሙ። ሥምምነቱን የጤና ሚኒስቴር፣ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲና የሩስያ ፓን-አፍሪካ ፐብሊክ ፕራይቬት አጋርነት ለልማት የተሰኘ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ተወካዮች ፈርመውታል። የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ በዚህ ጊዜ፤ በሥምምነቱ መሠረት ፕሮጀክቱ ለአምስት ዓመታት እንደሚቆይና 2 ሺህ የጤና ማዕከላትን ለመገንባት…

Read More

የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች ረቂቅ አዋጅ የሲቪል ሰርቪሱን የማስፈጸም አቅም ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት ያስችላል

የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች ረቂቅ አዋጅ የሲቪል ሰርቪሱን የማስፈጸም አቅም ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታትና ምርታማነትን ለመጨመር እንደሚያስችል ተመላከተ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ኃብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010ን ለማሻሻል በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ የባለድርሻ አካላት ውይይት መድረክ አካሂዷል። የአዋጁን ማሻሻል አስፈላጊነት፣ ዓላማ፣ ይዘት፣ ተፈጻሚነትና ሌሎች አጠቃላይ የአዋጁ ድንጋጌዎች…

Read More

ከተቋቋመ በአንድ ወር ውስጥ 8 ሺህ ቶን ቡና ወደ ማዕከላዊ ገበያ ሸኝቷል፦ የቦንጋ ምርት ጥራትና ሴርትፊኬሽን ማዕከል

ቡና ብዙ ተጠቃሚ ካላቸው እና ብዙ ጥቅም ላይ ከሚውሉ መካከል አንዱ ነው፡፡ አሃዛዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩ ከሆነ በዓለም ላይ በቀን በጣም ብዙ የሚባል ሲኒ ቡና ተጠቃሚ እንደለው ነው የሚነገረው፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያም አሁን አሁን በየቦታው የጀበና ቡና ቤቶች ተከፍተው ይገኛሉ፡፡ ይህም ስራ ዕድል መፍጠሩ አንዱ ነገር ሆኖ ሳለ ከዚህም በተጨማሪ ቡና በሀገር ደረጃ ምን ያህል ተጠቃሚ እንደለው…

Read More

በጤና ተቋማት ፍትሀዊና ጥራቱን የጠበቀ የጤና አግልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የለውጥ ትግበራን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የጤናው ስርዓት አዳዲስ ፈጠራዎች መመሪያ፣ ውጤታማ አመራር እና ተጠያቂነት፣ የጤና ተቋማት ልዩ እውቅና አሰጣጥ ፍኖተ ካርታ እና በመጀመሪያ ደረጃ አሀድ ጤና ተቋማት የአሰራር ስርዓት ማነቆዎች ላይ ያተኮረ ሪፎርም ክልላዊ ይፋዊ ማስጀመሪያ ፕሮግራም በሚዛን አማን ከተማ እያከናወነ ይገኛል። በመድረኩ የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ዶ/ር…

Read More

ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የኮይሻ- ኦሽካ ዴንቻ ጠጠር መንገድ ግንባታ መርቀው ከፈቱ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በ78 ሚሊዮን ብር ወጭ የተሰራውን የኮይሻ-ኦሽካ ዴንቻ ጠጠር መንገድ ልማት ፕሮጀክት መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል። 44 ኪ.ሜ ርቀት ያለው ጠጠር መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በክልሉ መንገዶች ባለስልጣን ታርጫ ዲስትሪክት ጽ/ቤት የተሰራ ሲሆን ኮንታ ዞን ኮንታ ኮይሻ ወረዳ ኮይሻ ከተማን ከኦሽካ ዴንቻ ቀበሌ ጋር የሚያገናኝ…

Read More

ኢትዮጵያ በብሪክስ ውስጥ ተጠቃሚነቷ እንዲረጋገጥ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን በጥናት ለመደገፍ እየተሰራ ነው

ኢትዮጵያ በብሪክስ ውስጥ በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ተጠቃሚነቷ እንዲረጋገጥ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን በጥናት ለመደገፍ እየተሰራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ገለጸ። በኢንስቲትዩቱ የኤዥያና ፓሲፊክ ጉዳዮች ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር ጄኔራል አንተነህ ጌታቸው(ዶ/ር) በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የጋራ ተጠቃሚነት መርህ አንዱ ነው ብለዋል። ይህንን ከግምት በማስገባት ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ ብሔራዊ ጥቅምን ከማስከበር ጎን ለጎን የጋራ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳለው…

Read More

ከተረጂነት አስተሳሰብ ለመውጣት ተረጂነትን የሚጸየፍ ትውልድ ሊኖር ይገባል። ዶክተር ሰማ ጥሩነህ።

ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለሀገር ክብር በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የነበረው ህዝባዊ ውይይት ተጠናቋል። በውይይቱም ሰነድ ቀርቦ ተሳታፊዎች ውይይት በማድረግ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ከተሳታፊዎች መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት ከተረጂነት ለመላቀቅ ወደ ስራ መግባት ይኖርብናል ሲሉ ተናግረዋል ። አሁን ላይ ከሚያርሰው ይልቅ የሚቀመጠው በዝቷል ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ እጅ ለእጅ በመያያዝ ወደ ልማት ልንመለስ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል ። ስራ…

Read More