Trendings

Getenesh Gebeyehu

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ገቢዎች ቢሮ ከ7ሺህ7መቶ በላይ ዜጎች የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል- አቶ ወንዱ ታደሰ

የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱን በማዘመን ረገድ አይነተኛ ሚና እንዳለው አቶ ወንዱ ታደሰ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ምክትል የቢሮ ኃላፊና የደንበኞች አገልግሎት የገቢ አሰባሰብና አወሳሰን ዘርፍ ኃላፊ ተናግረዋል፡፡ አቶ ወንዱ ታደሰ የደንበኞች አገልግሎት የገቢ አሰባሰብና አወሳሰን ዘርፍ የግብር ከፋዩን መረጃ ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ በማደራጀትና ቴክኖሎጂ በመጠቀም ዘመናዊ የገቢ አሰባሰብ ስርዓት በመገንባት የክልሉን መንግስት ወጪ…

Read More

በጎነት ትልቁ የሰብዓዊነት መገለጫ፣መሰጠትን የሚፈልግ ሰናይ ተግባር ነው። ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሴቶች የየ2016 ዓ/ም የክረምት በጎ ፈቃድ መክፈቻ ፕሮግራም በሚዛን አማን ከተማ ተካሂዷል ። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በመክፈቻው ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር በክልሉ በርካታ ቁጥር ያላቸውን በጎ ፈቃደኞች በማሳተፍ በችግር ውስጥ ያሉ ወገኖችን መርዳት መቻሉን ተናግረዋል ። በጎነት ትልቁ የሰብዓዊነት መገለጫ፣መሰጠትን የሚፈልግ ሰናይ ተግባር ነው። በሁሉም አካባቢዎች…

Read More

የፖለቲካ ፓርቲዎች ግኑኝነት መጠናከር የፖለቲካ ልምምድ መሻሻል ውጤት ነው፦ አቶ ሰለሞን አየለ

የፖለቲካ ፓርቲዎች እርስበርስ ግኑኝነት መጠናከር የፖለቲካ ልምምድ መሻሻል ውጤት መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢና የካፋ አረንጓዴ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ሰለሞን አየለ ገለጹ። በክልሉ ህጋዊ ፍቃድ አግኝተው የሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ጥምረት ምክር ቤት አባላት በካፋ ዞን ሸሾንዴ ወረዳ የተሰሩ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ተዘዋውሮ እየጎበኙ ይገኛል። የፖለቲካ ፓርቲዎች እርስበርስ…

Read More

በየደረጃው ያሉ የአስተዳደር እና የጤና ተቋማት የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትን ለመቀነስ በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለጸ።

በክልሉ የኤች አይቪ ኤድስ ስርጭትን ለመቀነስ በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ የክልሉ ጤና ቢሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር ያደረገው ምክክር ተጠናቋል። በምክክሩ መድረክ በክልሉ የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ ከተማ አስተዳደሮችና ወረዳዎች የአፈጻጸም ሪፖርታቸውን አቅርበው አስገምግመዋል። በቀረበው የአፈጻጸም ሪፖርት ስርጭቱን ለመቀነስ ጥረቶች መኖራቸውና አሁንም ቅንጅታዊ አሰራሮች ይበልጥ የሚዳብሩበት እንደሆነም በመድረኩ ተነስቷል። ሪፖርት ከቀረቡባቸው ከተማዎች በተለይም…

Read More

32ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 32ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ 1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅን ለማሻሻል በቀረበ አዋጅ ላይ ነው፡፡ ከህጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማዕቀፍ ውጪ የቆዩ የፖለቲካ ቡድኖች በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ፍላጎት በሚያሳዩበት ጊዜ እነዚህን አካላት ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ አድርጎ…

Read More

የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የገለጻና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እያካሄደ ነው

የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው የምክክር ምዕራፍ እንዲሁም ቀጣይ ውይይቶችን አስመልክቶ ለባለድርሻ አካለት ገለጻና የገንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እያካሄደ ነው። በመድረኩ የፓለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ ምሁራን፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትና ማኅበራት ተወካዮች፣ ከሦስቱ የመንግሥት አካላት የተወከሉ ተወካዮች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። ግንቦት 21 ቀን 2016 በአዲስ አበባ የተጀመረው የምክክር ምዕራፍ ከጠዋቱ መክፈቻ…

Read More

በቀጣዮቹ 10 ቀናት በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች የተሻለ የዝናብ ስርጭት ይኖራል- ኢንስቲትዩቱ

በሚቀጥሉት አሥር ቀናት በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች የተሻለ የዝናብ መጠንና ስርጭት እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። በዚሁ መሰረት በሚቀጥሉት አሥር ቀናት ምሥራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ጅማ፣ ኢሉአባቦር፣ ማዕከላዊ እና ምዕራብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ አሶሳ፣ ካማሺ፣ መተከል እና የማኦ ኮሞ ልዩ ዞን የተሻለ የዝናብ መጠን እንደሚኖራቸው የኢንስቲትዩቱ መረጃ አመላክቷል፡፡…

Read More

የፍትህ ዘርፍ ሪፎርም የመንግስት ዋነኛ የትኩረት አጀንዳ ነው ፦ አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ

የፍትህ ዘርፍ ሪፎርም መንግስት ትኩረት የሰጠው ዋነኛ የትኩረት አጀንዳ መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለጹ። የሀገራዊ የፍርድ ቤቶችና የፍትህ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን የ2016 በጀት ዓመት የ9 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ነው። የመድረኩ አላማ የአፈጻጸም ሂደቱን በመመልከት የመጡ ለውጦችን እና ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል። አፈ ጉባኤ አቶ…

Read More

የህብረተሰብ ተወካዮች በአጀንዳ ሃሳቦች ላይ እያደረጉት ያለው ውይይት እንደቀጠለ ነው

ሁለተኛ ቀኑን ያስቆጠረውና የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ እያስተባበረ የሚኘው የምክክር ምዕራፍ ዛሬም ቀጥሏል፡፡ ከትናንት ግንቦት 21 ቀን 2016 ከሰዓት በኋላ ጀምሮ በነበረው መርሃ-ግብር ተሳታፊዎች በየህብረተሰብ ክፍላቸው በቡድን በመሆን ከወከሉት ማህበረሰብ በአደራ ያመጧቸው የአጀንዳ ሀሳቦች ላይ ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ በሂደቱ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የኛ የሚሉትን እና የተስማሙባቸውን የአጀንዳ ሀሳቦች በማጠናቀር ለኮሚሽኑ በቃለ-ጉባኤ ተፈራርመው…

Read More

የኮንስትራክሽን ዘርፉ በመሠረተ ልማትና በሥራ ዕድል ፈጠራ ትልቅ ሚና እየተጫወተ ነው – አቶ ተመስገን ጥሩነህ

ኢትዮጵያ ውስጥ የኮንስትራክሽን ዘርፉ በመሠረተ ልማትና በሥራ ዕድል ፈጠራ ትልቅ ሚና እየተጫወተ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ 2024” የተሰኘ ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ አውደ ርዕይና ሲምፖዚየም በሚሊኒየም አዳራሽ ዛሬ መርቀው ከፍተዋል። “ኢትዮጵያን እንገንባ” በሚል መሪ ኃሳብ በሚካሄደው አውደ ርዕይ መክፈቻ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ…

Read More