Trendings

Getenesh Gebeyehu

ከሰል ማጠቢያና ማበልጸጊያ ፋብሪካ በዳውሮ ዞን፦

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብዙ የማዕድናት ክምችቶች ያሉበት ክልል ነው። ክልሉ በበርካታ የተፈጥሮ ሀብቶች የበለጸገ ነው፡፡ በክልሉ ከፍተኛ ክምችት ያለው የማዕድናት ሀብት ይገኛል፡፡ እንደ ወርቅ ያሉ የከበሩ ማዕድናት፣ ለኢንዱስትሪ፣ ለኮንስትራክሽን እና ለመሳሳሉት በግብአትነት ሊውሉ የሚችሉ እንደ ድንጋይ ከሰል ያሉ በርካታ ማዕድናት በስፋት ይገኛሉ ፡፡ ክልሉ በአሁኑ ወቅት በተለይ በድንጋይ ከሰል ማዕድን ባለቤትነቱ ብቻ ሳይሆን…

Read More

በጥናትና ምርምር የተለዩና የተሻሻሉ ዝርያዎችን በማስፋፋት የአርሶአደሩን ተጠቃሚነት ማሳደግ ይገባል ፡፡ አቶ ማስረሻ በላቸው

በጥናትና ምርምር ስራዎች የግብርና ምርታማነት ማነቆዎችን በመፍታት የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ማሳደግ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ድጋፍ በዳሰሳ ጥናት በተለዩ የግብርና ልማት ማነቆዎችና በቀጣይ አቅጣጫ ዙርያ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ አካሂዷል። በምክክር መድረኩ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ…

Read More

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ዋና አፈጉባዔ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ እንኳን ለቤንች ብሔረሰብ ዘመን መለወጫና ምስጋና በዓል “ቢስት ባር ” በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።

ዋና አፈጉባኤ ወንድሙ ኩርታ የቤንች ብሔረሰብ የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል “ቢስት ባር” መከበሩ ክልሉ ለባህል መጎልበት የሰጠውን ትኩረት ማሳያ ነው ብለዋል። የክልሉ መንግስት የብሔሮች ብሔረሰቦች ባህል ጎልቶ እንዲወጣ፣እንዲለማና ጥቅም ላይ እንዲውል በትኩረት እየሰራ ይገኛልም ብለዋል በመልዕክታቸው ። የቤንች ብሔረሰብ የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል “ቢስት ባር” ቀደምት አባቶች ያቆዩትና በመሀልም ተረስቶ ለዘመናት ሳይከበር እንደቆየም አስታውሰዉ አሁን…

Read More

የሲንጋፖር ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

የሲንጋፖር ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድል በመጠቀም በኢትዮጵያ በግብርና እና ሌሎች ዘርፎች ኢንቨስት እንዲያደርጉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ጥሪ አቀረቡ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሲንጋፖር ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሲንጋፖር አቻቸው ቪቪያን ብላከሪሽናን (ዶ/ር) ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል። በውይይታቸውም በሀገራቱ መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው እንዲሁም የጋራ ትብብርን…

Read More

ኢንስቲትዩቱ የቲቢ ህክምናን ከ24 ወራት ወደ 9 ወራት ዝቅ የሚያደርግ የምርምር ውጤት ማግኘቱን አስታወቀ

የአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት 24 ወራት ይወስድ የነበረውን መድሃኒት የተላመደ የቲቢ ህክምናን ወደ ዘጠኝ ወራት ዝቅ የሚያደርግ የምርምር ውጤት ማግኘቱን አስታውቋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ 54ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ያዘጋጀው የጉባኤና ጉብኝት መርሃ ግብር የጤናው ዘርፍ ባለድርሻ አካላት፣ የልማት አጋሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተካሂዷል። መርሃ ግብሩ ኢንስቲትዩቱ በምርምር ያለው አበርክቶና በሚያከናውናቸው ስራዎች ዙሪያ ገለጻ በማድረግ…

Read More

የብዙ ዉብ ባህሎችና ተፈጥሮ ሃብቶች ባለቤት፣ ምዕራብ ኦሞ ዞን

ምዕራብ ኦሞ ዞን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከሚገኙ ዞኖች አንዱ ሲሆን ብዙ ባህሎች፣ወጎች፣ተፈጥሮ ሀብቶችና ለቱሪዝም ምቹ የሆኑ ድንቅ ገጸ በረከቶች ያሉት አካባቢ ነዉ። ዞኑ ከፊል አርሶአደርና አርብቶአደር ማህበረሰቦች የሚገኙበት መልከ ብዙ ዞን ነዉ። በዞኑ ውስጥ የሚገኙ የብሔረሰቦች ቱባ ባህሎች በራሳቸው የቱሪዝም መስህብ መሆን የሚችሉ በመሆናቸዉ የማልማት፣የማስተዋወቅና የመንከባከብ ስራ ይፈልጋል። የምዕራብ ኦሞ ዞን ባህልና ቱሪዝም…

Read More

የጃንቹ ተራራና የሙዝ ደን

የወረዳው ሕዝብ የመንግስትን የልማት አቅጣጫ ተቀብሎ የመተግበር ልምድ ያዳበረ ለመሆኑ ማሳያ ነው። የቤንች ሸኮ ዞን በሁሉም ወረዳዎቹ ተመሳሳይ ምርት የሚመረትበት ነው። ይህ የሙዝ ምርት የሚዛን አማን ከተማን ጨምሮ በሌሎች ወረዳዎችም ይመረታል። የምርቱ መጨመር የአካባቢ የሙዝ ገበያን አረጋግቷል። ለአብነትም በሚዛን አማን ከተማ አራቱ በ20 ብር ሲሸጥ የነበረ የበሰለ ሙዝ አሁን በግማሽ ቀንሶ በ10 ብር እየተሸጠ ነው።…

Read More

ለቤንች ብሄር ዘመን መለወጫና ምስጋና በዓል (ቢስት ባር ) የቅድመ ዝግጅት ስራ መጠናቀቁ ተገለጸ።

ከግንቦት 29 እስከ ሰኔ 01 2016 ዓ ም በድምቀት ለሚከበረው የቤንች ብሄር ዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል ቢስት ባር የቅድመ ዝግጅት ስራው መጠናቁን የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የበዓሉ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሀብታሙ ካፍትን ገለጹ። የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ በዓሉን ለማክበር በተሰሩ ስራዎች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል። የቤንች ብሄር ዘመን መለወጫና ምስጋና በዓል ቢስት ባር ከዚህ ቀደም ሲከበር…

Read More

በደን ተኮር የህብረተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራሞች በመታገዝ በማር ምርት የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተሰራ ነው::

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ደን ፣አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ በደን መመናመንና መጨፍጨፍ የሚከሰቱ አማቂ ጋዞች ቅነሳ ፕሮግራም ( REED+) ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በደን ተኮር ኑሮ ማሻሻያ አማራጮችና ንብ ማነብ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫና የልምድ ልውውጥ በቦንጋ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል፡፡ በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ…

Read More

በዘንድሮ የመኸር ምርት ዘመን በክልሉ ከ391 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በማልማት 17 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት ይሰራል፡- አቶ ማስረሻ በላቸው

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ የ2015/16 ዓ.ም የመኸር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2016/17 ዓ.ም የመኸር ንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል። በንቅናቄው መድረክ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው የልማት በክልላችን ግብርና ምርትና ምርታማነትን የሚያሻሽሉ ተግባራት መከናወን በመቻላቸው ባለፉት ሁለት ዓመታት በግብርናው ዘርፍ እምርታዊ ለውጥ እየመጣ ያለ…

Read More