በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምልከታ በተደረገባቸው ዞኖች ያለው የግብርና ግብኣት አቅርቦትና ስርጭት የሚበረታታ መሆኑ ተገለጸ ።
በኢፌዴሪ ግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የተውጣጡ የኢንስፔክሽን ቡድን በካፋ ዞን ጊንቦ እና ዴቻ ወረዳዎች ምልከታ አድርገዋል። የኢንስፔክሽን ቡድኑ በዞኑ ተዘዋውሮ በተመለከተባቸው ወረዳዎች የቀረቡ የግብርና ግብኣት አቅርቦት ስርጭት ለበልግ የእርሻ ወቅት በተገቢው ስርጭት መካሄዱን መመልከታቸዉን የቡድኑ አስተባባሪ ወ/ሮ አልማዝ ወዳጆ ተናግረዋል ። በአንዳንድ ቀበሌዎች የሚታየው የመንገድ መበላሸት ከወቅቱ የዝናብ ሁኔታ ጋር ተግዳሮት እንዳይሆን ከወዲሁ ሊታሰብበት…
